Get Mystery Box with random crypto!

ጠበል ማይፈውሰው መፅሐፉን ደግመው ጠበሉን ቀደሱት ልቤን ያሰረውን ፍቅሯንም ገፀሱት በአብ ወል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጠበል ማይፈውሰው


መፅሐፉን ደግመው ጠበሉን ቀደሱት
ልቤን ያሰረውን ፍቅሯንም ገፀሱት
በአብ ወልድ አያሉ ደጋግመው ባረኩኝ
ጠበል አየረጩ አሳስረው ጠመቁኝ

ግና ዘንግተዋል
ሳያውቁት ኑረዋል
ፍቅሯን ለማስለቀቅ አባት ሆይ ጥረዋል
ጠበሉን ደግመዋል
ባራቱም መዓዘን ሶስት ጊዜ ባርከዋል
እንኳን ሊያጠፉልኝ ጭራሽ ጨምረዋል
በደገሙት መፅሃፍ
በባረኩኝ መስቀል
በጠመቁኝ ጠበል
በሽታዬ ለቆ ፍቅሯ ብቻ ቀርቷል
እንኳን ሊያጠፉልኝ ይባስ ጨምረዋል


ዮኒ
ኣታን @yonatoz


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19