Get Mystery Box with random crypto!

ሳሊዝሽ ላጣሁሽ አቤል ዩሐንስ የመጨረሻዬ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሳሊዝሽ ላጣሁሽ
አቤል ዩሐንስ


የመጨረሻዬን
ላንቺ ሚሆን ብዬ ፤ ይህን እፅፋለሁ
ልብን የሚነድፍ ፤ ዜማ እየሰማው
ምስልሽን ደግሜ
ላላየው እየማልኩ ፤ በሃሳቤ እስላለው
ስዬ እንዳበቃው ፤ እንዲ እለዋለው

የኔና ያንቺ ዳር ፤ ማብቂያው ተበጅቶ
ያንቺ መንገድ ሲሄድ ፤ ከኔ ተለይቶ
እንደ ፍቅረኛሞች ፤ ልንተያይ ቀርቶ
ስምሽ ባለሁበት ፤ ከጎኔ ሲነሳ ፤
ያስደነግጠኛል
የኔን የጠሩብሽ ፤ ያስታወሱሽ ለታ
ለሊቱን በሙሉ ፤ ቅዠት ይታይሻል
በአፍላ እድሜያችን ፤ የፀነስነው ፍቅር
መካን አደረገን ፤ ሲጨነግፍብን

አንቺስ በመንገድሽ ፤ አፍቃሪሽ ሙሉ ነው
ለምን ይመስልሻል ?
ለኔ
ቁንጅናሽ ፍርድ ነው
አይኔ ላይ ተስሎ ፤ ልቤን ይደቃኛል
በእንባዬ ጠብታ ፤ ፀፀት ባህር ሰርቶ
ወስዶ ያሰጥመኛል
ድምፅሽ ይመረኛል
ያልሽውን ስደግም ፤ ይቆመጥጠኛል
እጅሽ ሰንሰለት ነው
እስካሁን አስሮኛል
በኔ ምክንያት አሮ
የሳሳው አንጀትሽ ፤ እረግሞኛል መሰል
እህል ውሃው ሁሉ ፤ ገብቶ ይክደኛል

ለካ
ፍቅር ጊዜው ሲቋጭ ፤ ያለፈው ያስቆጫል
ጥዑም ያሉት ትናንት ፤ ዛሬ ላይ ይመራል
አንቺስ እረስተሽው ፤ ሰው አለ ከእቅፍሽ
ይብላኝ እነጂ ለኔ ፤ ላሊዝሽ ላጣሁሽ



ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19