Get Mystery Box with random crypto!

አበባዬ አብቅቷል ።።።።።።።።።።።።።።።። እቤቴ ፊት ለፊት ጽጌሬዳ ተከልኩ አንድ ቀን በድንገት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አበባዬ አብቅቷል
።።።።።።።።።።።።።።።።
እቤቴ ፊት ለፊት ጽጌሬዳ ተከልኩ
አንድ ቀን በድንገት ትመጫለሽ እይልኩ
ከቀን ቀን ተተካ አበባው ደረሰ
መምጣቷም ሳይጠብቅ እየገሰገሰ
ቀናቶች አለፉ በሺህ በእልፍ አእላፍ
የልቤ ተስፋ ግን ከቦታውም ሳያልፍ
ቀኑ ደረሠና አበባው አፈራ
ልክ አንቺን ይመስላል ቀጭለማ ሚያበራ
አበባው ሊሞት ነው ቀናትም አልቀረው
ይንቺ መምጣት ከቶ ሀሳቡም ያሎነው
አበባው ቢደርቅም ማፍራቱ አቁሞ
ቢቻው ሆኖ ባየው ተስፋውም ጨልሞ
የኔ ልብ እዛው ነው ተስፋው ማይገታ
ትግስት ተችሯል ከፈጣሪ ጌታ



በቶኒ ይፋቱ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19