🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አንከፋፋለም ወንድም ወንድሙን አይከስም እህት እህቷን አትገልም ይህን አቃለው ሀገሬ.. የገባው ሴ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንከፋፋለም

ወንድም ወንድሙን አይከስም
እህት እህቷን አትገልም
ይህን አቃለው ሀገሬ..
የገባው ሴጣን ሚወጣው
እኛ አንድ ላይ ስንሆን ነው
አደለም አብረን በኖርነው
አንድ ማዕድ ላይ በቆምነው
ኑሮ መስርተን ተጋብተን
ሰይጣን ገብቶ ነው እመነን
እንደዚ የተራራቅን
አምናለው ነገሩ ያልፈል
ክፋታችን ይጠፋል
ወንድም ወንድሙን ያቅፈል
ሀገሬው ፍቅር ይሰብካል
ሁሉም በኛ ይቀናል
አለም ወደኛ ይመጣል
ቀኝ ሳንገዛ የኖረነው
ላንከፋፋል እኮ ነው
እናም ወንድም ጓዴ
ጠላት የሆንከኝ ዘመዴ
እኔ ይቅር ብያለው
ካንተ ዘንዳ እንዴት ነው

ሐና ይመር
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19