🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አሁን ግን አልቻልኩም ትዝ ይልሃል ውዴ ያኔ ስንጀምር ገና ከቤቴ በራፍ ራቅ ብዬ ወደታች ስታ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አሁን ግን አልቻልኩም
ትዝ ይልሃል ውዴ
ያኔ ስንጀምር ገና
ከቤቴ በራፍ ራቅ ብዬ ወደታች
ስታየኝ ስመጣ ከቤቴ በታች
ጠርተኸኝ ነበር ደስ በሚል ቃና
መልስ ሳልሰጥ ስቀር ጠራኸኝ እንደገና
ዞር ብዬ ሳይህ ልቤ ድንግጥ አለና
ተሸነፈልህ በፍቅርህ ወደቀና
ለመግደርደር ግና
እምቢ አልኩ ሸሸው ወደኃላ
የሴትነት ወጉ እንዳይቀር እንዳይጉላላ
በብዙ ጥረት ተገናኘህ ከልቤ
ገባህ ከቀልቤ
ፍቅርህ ሆነ ቀለቤ
ተላምደን ብዙ ቆየህ ካጠገቤ
ሀገር ጉድ አለ በሁለታችን መዋደድ
ትዝ ዪልሃል ውዴ
አንተን ለማግኘት ስመጣ ይረዝም ነበር መንገዴ
ይጠነክር ይፀና ነበር መውደዴ
ግና ምን ያረጋል
አልሆነም ያስጠላል
እጅጉን ተቀያይመናል
በአንዳች ምክንያት ተኮራርፈናል
በአንዳች ምክንያት ተጣልተናል
ጥለኸኝ ሄደሃል
ደግሞም ተለያይተናል
አሁን ግን አልቻልኩም
አበባዬ በሀሳቤ አልፀናውም
እንደ ተውከኝ አይደለሁም
ወደዛ ወደ እሩቅ ቦታ ጥለኸኝ ሄደሃል
ቤቴም ቀዝቅዟል እንደ በረዶ
ልቤም ሆኗል ባዶ
ፍቅሬ እንዲያ ሰው ጉድ እንዳላለ
እንዲያ በፍቅራችን እንዳልተደሰተ
በመዋደዳችን እንዳልተገማመተ
የኛን ፍቅር እያዩ በእነሱ እንዳላፈሩ
አንድ በመሆናችን እንዳልኮሩ
እስቲ ዛሬ በመኩሪያቸው ይፈሩ
አንለያይም ብለህ ነበር ለኔና ለሰፈሩ
አንድ እንደሆንን አውቆ ነበር ሀገሩ
ፍቅሬ ለምን ታዲያ በኔ ጨከንክ
አብረኸኝ ላትሆን ለምን እኔን አፈቀርክ
ምንስ ብንጣላ
ምንስ እንኳን ብንኳረፍ
ይቅርታ ወዴት ገባ
ፍቅር ሆዴ ባባ
አረ ሆዴ ተጨነኩ
በጣም ከልቤ አዘንኩ
ያቺ ሳቂታዋ ልጅ አኮረፍኩ
ግን ብትመጣ ውዴ
ደስ ትሰኛለች ልቤ
ትረጋጋለች ቀልቤ
ፍቅር ይሆናል ቀለቤ
እባክህ ናልኝ ሁን እንዳሳቤ
እኔ ናፍቆኛል መገኘት በቀጠሮ
እንዴት አደርክ አደርሽ መባባል
ጠዋት ማታም መሳሳም
ናፍቆኛል ጭቅጭቅ ንትርኩም
በአንድ ልብ መተቃቀፍ
በአንድ ሀሳብ መክነፍ
እና ውዴ ካለህበት ከዛ ከሩቅ ቦታ
ናና እየኝ ለአንድ አፍታ
ናልኝ የኔ ሸጋ
ጥፋቴ ጥፋትህን እንድናወጋ
ይቅር እንባባል እባክህ ናልኝ ሁን ከኔጋ

በሜሮን ሲሳይ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19