🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ወንድ ሲያለቅስ አንቺ ከኔ የሄድሽ 'ለታ ልቤ አይጀግን ክንዴ አይረታ በማለዳ፤ ካድማሱ ላይ ስትው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ወንድ ሲያለቅስ

አንቺ ከኔ የሄድሽ 'ለታ
ልቤ አይጀግን ክንዴ አይረታ
በማለዳ፤
ካድማሱ ላይ ስትውል ጸሃይ
ፍም ጉንጭሽን
ከሷ ላይ ነው ስያት የማይ
ባመሻሹ፤
ከዋክብቱ ጨለማዬን ሲረብሹ
ንፁህ ፍቅር
ይታየኛል በጥል እድፍ መቆሸሹ

ለሊት ቅዠት፤
በቅንድብሽ ክራር ሰርተው ሲወድሩ
መላዕክታት ነይ እያሉ ሲዘምሩ
ነፍሴ አልቅሳ ስትከስሽ ለ እግዜሩ
ቁስል ዘርቶ
ከልቤ ላይ ሲከረቸም ናፍቆት በሩ

አታይም ወይ ወንድ ሲያለቅስ
ያቺን ምሽት
የጥል ግንቧን ሁሌ ስወቅስ
ምነው ዝም አልሽ?
ምነው አይንሽ ካይኔ ራቀ
ነይ እያለሽ
ዘመን ሲያለቅስ እምባ አጥቶ ነው የደረቀ

[ ቶማስ ትግስቱ ]

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19