🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ከሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመን አይሽሬ ውብ ግጥሞች መካከል አንዷን እንካችሁ ! 'የፍቅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመን አይሽሬ ውብ
ግጥሞች መካከል አንዷን እንካችሁ !
"የፍቅር ቃጠሎ"
(ገብረክርስቶስ ደስታ)
**********
ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ
እስረኛ ሆኛለሁ፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19