🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቆሜ ልመርቅሽ (ታደሰ ደምሴ) ሀገሬ.... ምጥሽ ቀላል ይሁን ትንሳኤሽ አይራቀን የጠላትሽን ሲቃ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቆሜ ልመርቅሽ

(ታደሰ ደምሴ)

ሀገሬ....
ምጥሽ ቀላል ይሁን
ትንሳኤሽ አይራቀን
የጠላትሽን ሲቃ፣
ባይናችን ያሳየን

ከአልፋ እስከ ኦሜጋ ኑሪ እንደተከበርሽ
ያ'በሻ አርማ ሊሆን ይሰቀል ሰንደቅሽ
ሞቶ "ኑሪ" የሚል ጀግና ይብቀልብሽ
ደግ ደጉን ብቻ ያርግዝ ማህጸንሽ
ከከሀዲ ልጅ ምጥ ማርያም ታገላግልሽ!!!
እስኪ አሜን በይ 'ባክሽ

@Maryam21161


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19