Get Mystery Box with random crypto!

አ፣ቡ፣ጊ፣ዳ ሀይሌ ከላይ ሁኖ: የኑሮዬ ካርታ: | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አ፣ቡ፣ጊ፣ዳ
ሀይሌ ከላይ ሁኖ: የኑሮዬ ካርታ:
ከእልፍኙ ገብቼ: ከኪዳኑ ዋልታ።
ጥበብን ከወረስኩ: ከ ሊቁ የኔታ:
አ፣ ቡ፣ ጊ፣ ዳ፣ ሆኖ : የሚስጥሩ ቋታ።
ከታችም ከላይም: ሁሉንም አጥንቼ:
የሰለስቱን ሚስጥር :ከአዳም ቀድቼ።

...ኮነ ከመ አሀዱ እምኔነ:

ብለው ሲጀምሩ ነፍሴ ተኮነነ።
ያ የኪዳኑ ቃል : በእምነት የታመነ:
የነፍሴን ቋጠሮ :በዕጣን ጢስ አፈነ።

ያውም ለቅዳሴው : አበው ላወረሱኝ
በዝማሜው ሰአት : ቀጠሮ አፈረስኩኝ:
ስምንትን ላላልፋት : ለዘጠኝ ታመንኩኝ።

@Kineeti

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19