Get Mystery Box with random crypto!

ስልጣን ስልጣን መጀመሪያ ከሁሉ አስቀድሞ የመላእክቶች አለቃ እንዲሆን ሳጥናኤል ተሾሞ ቀና ጓን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ስልጣን
ስልጣን መጀመሪያ ከሁሉ አስቀድሞ
የመላእክቶች አለቃ እንዲሆን ሳጥናኤል ተሾሞ
ቀና ጓንበስ ብሎ ያለበትን ቢቃኝ
ከስር መላእክቶች ከላይ ብቻዬን ነኝ
ብሎ አሰበና መላእክቶችን ሊያሞኝ
ሰበሰባቸው እና ብሎ ነገራቸው እኔ አምላካቹ ነኝ
መላእክት ሰሙና አሉ እንፀልይ
እንጽና ተባባሉ ባለንበት እንቆይ
የፈጠረን አምላክ ተገልጦ እስክናይ
ብለው ተቃወሙት እሄን አታላይ
ታድያ እሄን ሲሰማ የነሱን እንቢታ
ጦርነት ጀመረ እነሱን ሊመታ
ከአንዴም ሁለቴ መቶ ቢጥላቸው
ወደ እግዜር ለመኑ ሀይል እንዲሰጣቸው
ገብርኤለ ሚካኤል ሀይልን ተጫምተው
አሳስረው ጠፍረው ወደ ጥልቁ ወርውረው
እነሱ ከፍ አሉ እሱን ረግጠው
ስለዚ ሰው ሆይ ከሰይጣን ተማር
አባቶችን ስማ በነሱ ተመከር
ከኔ ሌላ የለም ብለ አትጓርር
ስልጣን የእግዚአብሔር ነው በልና ክበር
እሄንን ካላረክ አለና መወርወር
እግዝሄርን እሚፈራ ይከብራል ባንተ እግር።


ዬናስ