🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዓይኔን ጨፍኜ - እስከምከፍተው ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው አፌ ላይ ሳይደርስ -ያፈስኩት ቆሎ ስ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ዓይኔን ጨፍኜ - እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ -ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጓሮ ገብቷል -መርዶ ነጋሪ ።

እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
እርግብ መሬት ላይ- ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ምልቷል- በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል -በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሴጣን
ለመደነቂያ -ጊዜ ነው ያጣን።

በእውቀቱ ስዩም


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19