🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

< < ምንድን ነው ብሄሩ? > > ( (አራጋው ሙሃመድ) ) # Ethiopia አባቱ ወሎ ነው መካነ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

< < ምንድን ነው ብሄሩ? > >

( (አራጋው ሙሃመድ) ) # Ethiopia
አባቱ ወሎ ነው መካነ ሠላም
እናቱ ከጎጃም መርጦ ለማርያም
ጃንተከል ያደገች ጎንደሬ ናት ሚስቱ
የወለዱት ፍሬ ደቡብ ሆነ እድገቱ
ከለምለሟ ምድር አግብቶ ሲዳማ
ልጃቸው ለስራ ሄደ ወደ አዳማ
ካ'ሠላዋ ቆንጆ ተጋብተው ወለዱ
የነሱ ልጆችም በየአቅጣጫው ሄዱ
ትግራይ ሱማሌ አፋር ሄዱና ጋምቤላ
ተጋብተው ወለዱ አብሮ የሚበላ
አዲስ አበቤዎች ድሬ ላይ ፏ! ሲሉ
አፖስቶ ነው አቦ! ሀረሪ ባህሉ
ወሎ ከቤኒሻንጉል ልጅ ወልደው ካፈሩ
እስኪ የነሱ ልጅ ምንድን ነው ብሄሩ??

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19