🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ደስታ ግን ምንድነው ያለውስ ወዴት ነው ደስታን እሚሰጠው የሚያድልስ ማነው ከራስ እሚመነጭ ነውስ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ደስታ ግን ምንድነው ያለውስ ወዴት ነው
ደስታን እሚሰጠው የሚያድልስ ማነው
ከራስ እሚመነጭ ነውስ እሚሰጥ ነው ?
ሀዘን አስረስቶ ሰላም እሚያወርሰው
አረ እሱ ግን ማነው ከወዴትስ ነው ያለው
ጨበጥቁት ሳልለው ቶሎ እሚበተነው
እረዥሙን ጊዜ አጭር እሚያደርገው
ደስታ ግን ምንድነው ምንጩስ ከወዴት ነው
ደስታን ተቀብሎ እሚወስድብኝ
ደሞ ሲያስፈልገኝ እንካ እሚለኝ
በራሴ ደስታ ላይ እሚወስንልኝ
ለካ ሌላ አይደለም ደስታን እሚሰጠኝ
የደስታዬ ምንጩ እኔ እራሴ ነኝ
ታድያ እንዲ ከሆነ ደስታን ማን ነጠቀኝ
ብዬ ራሴን እንዲ ስል ወቀስኩኝ
ስለሌለኝ ትንሽ ስለጎደለኝ
ሁል ጊዜ በህይወቴ እያማረርኩኝ
ባለኝ በሞላልኝ ደሞም በተሰጠኝ
እግዚአብሔርን ካላመሰገንኩኝ
ያለኝ በቃኝ ብዬ ካልተደሰትኩኝ
የደስታዬ መጥፋት ተጠያቂ ነኝ ።

ዩናስ ጌታሁን
@Yoniiiiiiii7

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19