Get Mystery Box with random crypto!

#አልረሳህም #እንዴት #ይረሳኛል ውኃ ለመገደብ…በጥም የነደድከው ሀገር ልታበራ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#አልረሳህም
#እንዴት #ይረሳኛል
ውኃ ለመገደብ…በጥም የነደድከው
ሀገር ልታበራ… ራስህ የጨለምከው
#ባንተ_ነው_ያየሁት
በረሃ እያቀኑ … ከተማ ላይ መውደቅ
መሬት ላይ ተጥሎ…ሰው ልብ ላይ መፅደቅ
#ስመኘው #ነው #እንጂ
ከዬት አመጣለሁ…እንዳንተ አይነት ሀሞት
ልጆችህን ትተህ …… ለልጆቼ መሞት
ማያልፈውን ሕይወት…ለሚያልፈው ተራ ቀን
ርካሽ ፖለቲካ …… ውድ አንተን ነጠቀን
* * *
እንዴት ‘ረሳሀለሁ … ሀገር ሆኗል ስምህ
በልቤ ላይ በቅሏል … የጎፈረው ፂምህ
ትዝታና እውነትህ
ሀቅና አሟሟትህ … ሆዴን እንዲያባቡ
ዘወትር ፊቴ ላይ
ድቅን ትላለህ …… በሰበብ አስባቡ

ላልረሳህ ምያለሁ… ማስታወሴን ላልተው
ሞላ ሲሉኝ አንተ … በራ ሲሉም አንተው
===||===
ከሙሉቀን ሰ•


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19