Get Mystery Box with random crypto!

ባለ ዕፀ መሰውር ዕፀ መሰውርን ፣ ከደብተራ አግኝቶ ከሰው እንዲሰወር ፣ ገላውን ቀብቶ እንደ እ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ባለ ዕፀ መሰውር

ዕፀ መሰውርን ፣ ከደብተራ አግኝቶ
ከሰው እንዲሰወር ፣ ገላውን ቀብቶ
እንደ እግዜር ሳይታይ
በሚታይ ጎዳና
ወደ ባንክ ሄደና ፣
በንቁ ዘበኛ በሚጠበቀው በር
አልፎ ገንዘብ ሲዘርፍ አይታይም ነበር።
በዚህ ተደስቶ
ከዘላለም ቀንበር ፣ ካ'ይን ነጻ ወጥቶ
ግና ፣ ግና ፣ ግና
ተመልካች ባይኖረው ሆድ ነበረውና
እህል ወዳለበት በፍጥነት አቀና
ምግብ ቤት ሲገባ ፣ ማንም አልታዘዘው ፣ አይታይምና።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19