Get Mystery Box with random crypto!

#የመጠበቅ ስሌት ገደብን ሳስቀምጥ ለመጠበቅ ስሌት ልኬታ ሰጥቼ እድሜ ሳሰፍርለት ልቤ ሲያስቸ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#የመጠበቅ ስሌት

ገደብን ሳስቀምጥ ለመጠበቅ ስሌት
ልኬታ ሰጥቼ እድሜ ሳሰፍርለት
ልቤ ሲያስቸግረኝ እስከመቼ ብሎ
መድረሻው ሲናፍቀዉ በመጠበቅ ዝሎ

እኔ ግን
የዛለዉን ልቤን ቁስሉን እያከምኩት
ነቃ በል አትቁሰል እልፍ ጠብቅ አልኩት
የማያልቅ እልፍ ቀን የማያልቅ ነገ ነው
ለልቤ የነገርኩት ሞት ገደብ አልባ ነው

ምክንያቱም
የሁልጊዜ ኑሮ የላይ ጅማሮ ነው
ሞት የሚለው ኬላ ስዉር መንገድ አለው

እናም
እናም ተዉ አላልኩት ነገን ይጠብቃል
ጊዜ ግን ሞኝ ነው እንዲሁ ይነጉዳል
ህመሙን ደብቆ ብዙ ይጓጓል ልቤ
አያልቅም እያልኩት በደንብ አሳስቤ
እድሜዬን ገፍትሮ ችግሬን ረግጦ
ማጣቴን ሳይሰማ ከይመጣል ፈጦ
ዛሬን ይጠብቃል ነገንም ጨምሮ
በቃል ኪዳኑ ላይ እልፍ ቀንን አስሮ

ፅጌሬዳ አስናቀዉ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19