~~~~~~~ //~~~~~~~~~~~~~ "ሰው"ነት . . የቱርኩ ሶላቶ፤ ክብሬን ተመኝቶ፤ ሊበላኝ ጎምጅቶ ሊገዛኝ ሲቃጣው፤ አርፎ የተኛውን፤ የአንበሳ መንጋ ነብሩን አስቆጣው፡፡ ያ ነጩ ወንድሜ፤ ዘረኝነት አንቆት "ሰው"ነት ሲያማታው፣ ሰው መሆን የገባው፤ "እምዬ"ያሉት "ሰው" ዋጀኝ እንደገና እግረ ሙቄን ፈታው። "አሉላ" ያሉት "ሰው" ያ "ባልቻ" ያሉት "ሰው" በጦር በጎራዴ እያንገረገበ መገፋቴን ረታው፡፡ ክብር ሀገር ላቆዩልን ሁሉ ይሁን !!! .............. ................. ዐብይ ( @abiye12 ) ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 508 viewsAbela, 08:10