🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማነው ገላ ሻጩ ? __ እሷ ሰማይ ተደፍቶባት ከሰማዩ በታች ምድር ከእግሯ ርቋት መኖር አይሉት ኑ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ማነው ገላ ሻጩ ?
__
እሷ
ሰማይ ተደፍቶባት
ከሰማዩ በታች
ምድር ከእግሯ ርቋት
መኖር አይሉት ኑሮ
ኑራ የምታኖር
ባዶ ባደረ ሆድ
ባዶ ላደረ ሆድ
አልቅሳ ምታጎርስ
በእንባዋ ጠብታ
እንባን የምታብስ

እሱ
እምነቱን ገዝቶ
ውስጡን አሸብቶ
በሰከንዶች ስሜት
በሰከንድ ተገዝቶ
በጭኗ ያረፈ
ማእበሉን በእንባዋ
ተሻግሮ ያለፈ
ከሱ ጋ ተዋግቶ
በሱ የተሸነፈ
ታድያ ማነው ገላ ሻጩ
እራሱን አጉድሎ ጎዶሎን የመላ
ወይስ
በራሱ ስር ወድቆ
በጭኗ ያሽላላ።

ፀጋየ ግርማ(ሜሎስ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19