Get Mystery Box with random crypto!

#የጭፍን_እሩጯ ባለፍንበት ጉዞ በሄድንበት መንገድ አወይ አረማመድ አወይ መንገዳገድ በሞኝነት አለ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#የጭፍን_እሩጯ

ባለፍንበት ጉዞ በሄድንበት መንገድ
አወይ አረማመድ አወይ መንገዳገድ
በሞኝነት አለም የጭፍን እሩጯ
መተው ነበረብን ያልተገባ ምርጫ
ምንም ቢረፍድብን ቢዘገይም ሰአቱ
ነገ አዲስ ቀነው ይነጋል ሌሊቱ
ማመንታት በሌለው ህይወት ከቀጠልን
መልካሙን አቅርበን ክፊውን ካራቅን
ከፈጣሪ ታርቀን ሰላም ካወረድን
እንኳን አምላክ ቀርቶ ክፉ ጠላታችን
ፍቅራችንን አይቶ መልካም ይመኘልን።

ያንችው ታሜ
መጋቢት -30-2014ዓም 03:22
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19