🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ይሄ ሰው እብድ ነው፡፡ ( አብርሃም ሙሉ ሰው) እቤተክርስቲያን አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ሶላቱን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ይሄ ሰው እብድ ነው፡፡

( አብርሃም ሙሉ ሰው)

እቤተክርስቲያን
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ሶላቱን ሰገደ
እመስኪድ ፊት ቆሞ ፣
በትምህርተ መስቀል ፣ ተሳለመ ሄደ
ምንድነው ይሄ ሰው ፣ ሃይማኖት እምነቱ ?
በ'ሱ ልብ አንድ ሆነው ፣ ያፀኑት ሁለቱ
እሳት እና ውሃን
ውሃ እና እሳትን ፣ የያዘ አደባልቆ
ምን የሚሉት ጥበብ ፣ ከማን ዘንዳ አውቆ
ከአማኞች ተራ፣ ተለየ እርቆ ?
...
የኔ መንገድ ብቻ ፣የጽድቅ እየተባለ
ይሄ ሰው እንዴት ነው ፣
ከሁሉም ተስማምቶ፣ መከተል የቻለ ?
ሁለት እግር ያለው ፣ ሁለት ዛፍ ካልወጣ
አንደኛውን መምረጥ ፣ ሆኖ እድል እጣ
ወይም ሁሉን መተው ፣ አማራጭ እያለው
ለሁሉም የሚከብድ፣ ለብቻው ሚቀለው
ወላሂ ! ማርያምን ! ፣ ይሄ ሰው እብድ ነው ፡፡

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19