Get Mystery Box with random crypto!

ኑ ተቀራመቱ ! ''''''''''''''''''''' አንድ ቁራሽ ዳቦ ያጠግበኛል ብለው እዩ ሲቧቀሱ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኑ ተቀራመቱ !
'''''''''''''''''''''
አንድ ቁራሽ ዳቦ ያጠግበኛል ብለው
እዩ ሲቧቀሱ ከጓዳዋ ገብተው
ኑ ተቀራመቱ፣
ድርሻን ሊካፈል ነው ሁሉም ሰው ጉጉቱ
ከዚህ ቅንጣት እህል ምን እርባን ይገኛል?
የአንድ ዕለት ጉርሻ ስንት አመት ያጠግባል?
ለስንትስ ዘመናት ረሀብ ያርቃል?
ሰው ይጋደላል ወይ ለቁራሽ ጠበኛ
ይናዳል ወይ ካስማ ለአንባሻ ቅሚያ?
ብቻ ፣ ኑ ተቀራመቱ፣
ከጉርሻ ባታልፍም ዙሪያዋን ቀንጥቡ
ቁጭ ብለን ከምናይ ሆድ በከርስ ተክቦ
እኛም እንቃመስ ይቺን የሀገር ዳቦ።
'ካለም የተቀዳ ስንዝር መሬትሽን የሚሸነሽኑ
ከምኑ ምን ቆርሰው ከየቱስ ምን ሊያስቀሩ
የግማሽ ብርጭቆ ውሃ ለመጠጣት
ሸክላው ይሰበራል ከመጋፋት ብዛት
አትቀነጣጥቧት አትቦጫጨቋት
መልኳን አትደልዙ ይልቁን ጠብቋት
ትቀመጥ በመሶብ ትኑር ተዘልላ
ክብሯ ጌጧ ይሁን ታመስግን በተድላ
አትቀራመቱ !
እንኳን ሀገር ቀርቶ፣ አለምም አይበቃም ለሰው ልጅ ስፋቱ።

Nuniyat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19