Get Mystery Box with random crypto!

. ተወደድኩ እል ነበር ያዋራሁት ሁሉ በሳቀልኝ ቁጥር በድካም ህመሜ እልፍ ሰው ሲያ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

.


ተወደድኩ እል ነበር

ያዋራሁት ሁሉ በሳቀልኝ ቁጥር
በድካም ህመሜ እልፍ ሰው ሲያጣጥር

ተናፈቅኩ እል ነበር

ስሜን እየጠራ ጠፋህ ባለኝ ሁሉ
ሲያየኝ ፈገግ ባለ ባገር ሰው በሙሉ

ተገፋሁ እል ነበር

አስሬ የሳቀው ላንድአፍታ ቢዘጋኝ
ያቃሰተው ሁሉ ከጎኔ ቢጠፋኝ

ተሸነፍኩ እል ነበር

እንዴት ነህ? ባይ ባጣ ጧት ማታ ጠያቂ
ጠፋህ! የሚል ባይኖር እኩል ተብሰክሳኪ

አሁን ግን እላለሁ
ሁሉንም ስቻለሁ
ምክንያቱም አውቃለሁ
ይሄን ሁሉ የሆንኩት ዛሬ ላይ በእሷ ነው

በእሷ ስወደድ ነው መወደድ የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

መንሰፍሰፏ ስቦ ገዛኝ ከልብ መውደድ
ወደእሷ ያመራኝን መረቅኩት ያን መንገድ
ገና አሁን ተወደድኩ
ከአፌ ቃል ላይ ቀድማ ልቤን ሰማችልኝ
ቀልዱን ሳልኮምካት
ልነግራት ስላሰብኩ ፈገግ አለችልኝ

ይሄን ሁሉ አይቼ
እኔም ይሄን አልኩኝ ተወደድኩ እንደሰው
ተቅበዥባዡ ልቤን ፍቅር አለበሰው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ ስናፈቅ ነው ናፍቆት ቃሉ የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

በስልኳ ውስጥ ባዳመጥኩት በውብ ድምጿ በላከችው
በደብዳቤ በሰፈረ በቃሎቿ በሳለችው
ገባኝ መውደድ አየሁ ናፍቆት
መንሰፍሰፏ ልቤን ፍቆት
።።።፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ ስሸነፍ ነው መሸነፍ የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

ታገልኳት እንደሰው እጥላት መስሎኛል
እንኳንስ ልረታት
በቅጡ እንኳ ቆሜ መፋለም ከብዶኛል
አላወቅኩም ነበር መሰበር መሸነፍ
ሲነቁ መጋደም ቀና ሲሉ መክሸፍ
እሰይ ተማርኩላት ልኬን አሳየችኝ
ይሄው ወደቅኩላት እልል ረታችኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ ስገፋ ነው መገፋት የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

ልክ እሷ ስትገፋኝ
እስከዛሬ የወደቅኩት ህመም ሁሉ ለኔ አነሰ
የጨበጥኩት ህልሜ ሁሉ ከቅዠቴ ተላወሰ
በሷ ስገፋ ነው
የመገፋት ህመም ሰርስሮ የተሰማኝ
የመናቅ ትርጉሙ ሆድ ሆዴን የበላኝ
በሷ ስገፋ ነው
ያፈቀርኩት ቀኔ አመድ የሞላበት
ሁሉን ያለ ልቤ ፌዘኛ የዋለበት
በሷ ስገፋ ነው የተሰማኝ ይሄ ሁላ
ባዶ የሆንኩት ስም የሌለኝ ስሜት አልባ
ዋጋቢስ ነኝ የማልጠቅም የማልረባ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ'ኮ ነው ከ'ሀ' ጅምር
እስከ 'ለ' 'ሉ' ፊደል ድርድር
ቃል እያማጥኩ እየፃፍኩኝ የሰረዝኩት
ይሄን ግጥም ግጥም ብየ የጨረስኩት

የምር በእሷ
አይ እሷ!

በአቤኒ የተፃፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19