🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አ'ያ ዕድል ''''''''''' አንድ ሰሞን ቀን አንግሶ አንድ ሰሞን ቀን'ህ ሲሽር፤ እን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አ'ያ ዕድል
"""""""""""
አንድ ሰሞን ቀን አንግሶ
አንድ ሰሞን ቀን'ህ ሲሽር፤
እንደ ቀላል አነጣጥፎ
እንደ ቀላል ሲመነሽር!

አንድ ሰሞን ጊዜ አንስቶ
አንድ ሰሞን ጊዜ ሲጥል፤
እንደ ቀላል አሞጋግሶ
እንደ ቀላል ሲያብጠለጥል!

በአንድ ሁናቴ ዘመን ክቦ፥
እንደ አህያ አንከብክቦ፥
ፈጣሪህን አሸክሞ...
በሰዎች ልብስ ተረጋጠህ፥
በዘንባባው ተረማምደህ፥
ተብሎልህ "እልል እልል"፤
በማግስቱ በስልቻ
ትጫናለህ ኩንታል እህል!
#ዕድል

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19