🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሄደሽ ነበር ማንነቴን ንቀሽ በግጥሜ ተሳልቀሽ ባዶነቴን ነግረሽ ንፁህ ፍቅሬን ገፍተሽ ጨበሬ ነህ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሄደሽ ነበር


ማንነቴን ንቀሽ በግጥሜ ተሳልቀሽ ባዶነቴን ነግረሽ
ንፁህ ፍቅሬን ገፍተሽ ጨበሬ ነህ ብለሽ ከገደል አፋፍ ላይ ለብቻዬ ጥለሽ
ሄደሽ ነበር አይደል በእኔነቴ አፍረሽ
ሳስታውስ እንደውም ስቀልጅ በግጥሜ እንዲህ ነበር ያልሽው
ፊደልን አሰባጥሮ በቁሙ ደርድሮ
በላ ሞተ ጠጣ የግል ታሪክ ፈጥሮ
ሳነብለት ጊዜ መደበሪያ ሳጣ
የወደድኩት መስሎት ደስታው ቅጥ አጣ
ሰላሜን ነስተሽኝ ልቤን አቁስለሽኝ በጥያቄ አስረሽኝ
ሄደሽ ነበር አይደል ልፍስፍስ አድርገሽኝ
ገጣሚ ወጉ ነው የፀጉሩ መጨብረር
የአንገት ልብስ አርጎ በከተማው መዞር
ነይ እስኪ ቅረቢኝ ነይ እስኪ አስረጂኝ
እንዴት ለምን ሆኖ ግጥሜን ጠላሽው
ስሜት መተንፈሻ የተካበ ማንሻ መሆኑን እያወቅሽው
ሳልረሳው እዚጋ ውለታሽን ሁሉ እግዜር ይክፈልልኝ
ጥለሽኝ ስትሄጂ ዝና ያተረፈልኝ ከገደሉ አፋፍ ለሚሰኘው ፅሁፌ ምክንያት ሆንሽኝ
ሄደሽ ነበር አይደል አልወደውም ብለሽ
አልተውህም ያልሽኝ ቃልሽን ዘንግተሽ
እያልኩ እየነሳው ስህተትሽን የጥንቱን
አልወቅስሽም ከቶ እንዳንቺ አይደለሁም
ገጣሚ ጨበሬው ከገደሉ አፋፍ እንዲህ ልኮልሻል
ከልቡ ከሆነ የሰው ልጅ በፍቅሩ ገጣሚስ በፅሁፉ እንዴት ይጨክናል።


ሰላም (Selito)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19