🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

................... (ዮኒ-ኣታን) አትሰናበችኝ አትቀፊኝ ይቅር መመለስሽ ላይቀር | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

...................
(ዮኒ-ኣታን)


አትሰናበችኝ አትቀፊኝ ይቅር
መመለስሽ ላይቀር
ላይቀር መመለስሽ ሆዴን አታባቢው
አይኔን አታስነቢው
ልቤን አታስርቢው
አልሰቃይብሽ መጣው ብለሽ ሂጅ
ስንብቱ ይቅር ቻው ማለት አይበጅ።

የምን ስንብት ነው
የምን ቻው መባባል
እመጣለው ብለሽ መሄድሽ ይቀላል
የምን እንባ ማንባት
የምን መገላገል
ቀልብሽ እኔውጋ አይደል።

እዚሁ ቀልብሽ ጋ
አምሽተን ስንገባ
እንደኔ እና እንዳንቺ ፅዋ ስንጠባ
አመታት ቢነጉድም
የመምጣትሽ እንጂ
የመቅረትሽ መንፈስ በሃሳቤ አይሄድም።

አይገርምሽም...
አንዱ የኔ ቢጤ ጥላው ለሸፈተች
አስረሳኝ እያለ ፀሎቱን ያደርሳል
አንችዬዋ
ሰው እንዴት ወዳጁን ለመርሳት ይከሳል
እንጃ
ያስገርማል አይደል
አብሮ የበላን ሰው ለመርሳት መታገል...


ደግሞ ይሄን ሰሞን
ካንቺ ቀልብ ጋራ አየር ስንቀበል
እየተሳሳቅን
እየተቃቀፍን
አየተዛዘልን በፍቅር ስንበር
ያዩን ሰዎች ሁሉ ሲጠቋቆሙብን
እጅ በአፍ እያስጫንን
ውውው ይሄ ልጅ ለየለት ሲሉኝ
ቀልብሽን አቅፌ ቢያዩኝ
ይሁን ግድ የለንም
ችላ ብለን አልፈን
የሰው ጓሮ አበባ ቀጥፈን
ስንሯሯጥ ሲያባርሩን
ስንሯሯጥ ሲያባርሩን
ተዳክመው መች ያዙን...

ደግሞ አመሻሽ ላይ
ሬስቶራንት ገብተን
ሁለት ወይን አዘን
አንድ ለኔ አንድ ለቀልብሽ
ችርስ ለልቤ ችርስ ለልብሽ
ስታስቂኝ ሳስቅሽ.....

ሙቀቱን ለቆብን በዝናብ ሲክሰን
እንደተቃቀፍን ወርዶ ሲያበሰብሰን
ኮት ጃኬት አውልቄ ለቀልብሽ ሳለብሰው
ይጠቋቆማል ሰው።

ብቻ ተይው.....
መጣው ብለሽ ስትሄጅ
ቀልብሽን ሰጠሽኝ
ይባሱን ናፈቅሽኝ።


እንደ አላማ ስኬት እርካታ
በጨለማ ጮራዬን እይታ
ከከባድ ምጥ መገላገል
እፎይ እንደማለት ምንኛ መታደል
እየጠበኩሽ ነው ትመጫለሽ አይደል።

እጠብቅሻለው............

@yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19