🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

// አዳም ምን ይል ይሆን \\ የመጀመሪያው ሰው ዝንጀሮ ነበረ ከእለታት በኋላ እየተቀየረ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

// አዳም ምን ይል ይሆን \\
የመጀመሪያው ሰው
ዝንጀሮ ነበረ
ከእለታት በኋላ
እየተቀየረ እየተቀየረ
የፍጥረታት አባት
አዳምን መሰለ
ይህን አውቆ ቢሆን
አዳም ምን ይል ይሆን

ነጭነት ንጉስ ነው
ጥቁር ደግሞ ባርያ
ታላቅ ቋንቋ እንትን ነው
ታናሽ የነእንትና
በብሔር በጎሳ
በአገር ተከፋፍለን
ይህን አውቆ ቢሆን
አዳም ምን ይል ይሆን

ሰውና እንስሳ
አንድ ላይ ሲ፡ዳሩ
ወንድ ከወንድ ጋር
ሴት ከሴት እያሉ
ተፈጥሮን ታሪክን
እረስተው ሲኖሩ
እንትና ይገደል
ሺ አመት ይንገስ እሱ
የኔ አምነት ትክክል
ህግን እየጣሱ
ባልኖሩበት ሰአት
በታሪክ አሻራ ውለታ እየረሱ
በዛኛው ጊዜ ቂም
ዛሬን ሲያቆሽሹ
ይህን አውቆ ቢሆን
አዳም ምን ይል ይሆን

ልገምት

አዳም: ምን አቅም አለኝ እኔ
እንዴትስ ያምኑኛል
ፈጣሪ እንኳን መጥቶ
ሰቅለው ገለውታል

@abela_black

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19