Get Mystery Box with random crypto!

#እኔእራሴንየሆንኩኝለት ፡ ፡ ፡ እኔ እራሴን አይደለሁም፣ እያለውኝ ግን የለሁም። አጉል ጉራን ስቸ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#እኔእራሴንየሆንኩኝለት



እኔ እራሴን አይደለሁም፣
እያለውኝ ግን የለሁም።
አጉል ጉራን ስቸረችር ማልበገር ሲመስላቸው፣
በሆዴ ውስጥ ብዬ አውቃለው ባረገልኝ እንደ አፋቸው።
ክንብንቤን ገፈው ጥለው ማንነቴን ቢያስተውሉ፣
የኔስ ሕይወት ድብብቆሽ ከራሴው ጋር አኩኩሉ።


አንደበቴም አንድ ብሎ ዋሾነትን ከለመደ፣
ፍቅር ልቤን ስልብ አድርጎት እሩቅ ትቶኝ ከነጎደ፣
እምጥ ሰዶ ተንሰራፍቶ ናፍቆት ሥሩን ከዘረጋ፣
ውሸት ጉራን እየነዛው ስንቴ መሽቶ ስንቴ ነጋ።


ለሰው እንጂ ማስመሰሌ ዳሩ ለኔ ምን ፋይዳ አለው፣
ባደባባይ የሚቃጣኝ ጀግና ኩሩ ልብ እንዳለው።
ድንቄም ኩሩ ድንቄም ጀግና፣
ለነገሩ ማን አውቆብኝ እኔ እራሴን መች ሆንኩና።


እውነቱማ
ቁርሾ ዘልቆ መሀላችን ስንራራቅ ስንለያይ፣
ካንጀት ፈልቆ የሚፈሰው ሳቄም ሆኑዋል ካንገት በላይ።
እህል ውሀው አራቀኝም ሆዴም ጠግቧል ልቤ እርቦት፣
በሞላ ሰው አንቺን ይላል ጀሌ ጅጊ አጀብ ከቦት።
ትከሻዬ ምን ቢሰፋ መንፈሴ ግን ተሰበረ፣
ትዝታሽም ከጫንቃዬ እንደ ቋጥኝ ተከመረ።
ለነገሩ ምን ፋይዳ አለው፣
መች ለማለው መች ሰማለው፣
እኔ እራሴን እኮ አይደለው።


ወደ ራሴው ተመልሼ፣
ማስመሰሌን ከቀበርኩት ላያዳግም መሬት ምሼ፣
እውነት እውነት ፣
እኔ ራሴን የሆንኩኝ ለት፣
እሺታሽም ታክሎበት፣
ድሪቶውን ወዲያ ጥዬ ሀቁን ላንቺው ብናገረው፣
የፍቅራችን ዳግም ውልደት ያኔ ነበር ሚከበረው።


ለነገሩ ምን ሊጠቅም፣
አልናገር አልጋገር እኔ እራሴን ሆኜ አላውቅም።

#ሄኖክብርሃኑ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19