Get Mystery Box with random crypto!

መልከ ማክዳ ጸባየ ሰናይ እግርሽ የቀና ምድር ወሰማይ እንደኔ አይነቱ መንገደ መርገም ፍቅር ቢሰጥሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መልከ ማክዳ ጸባየ ሰናይ
እግርሽ የቀና ምድር ወሰማይ
እንደኔ አይነቱ መንገደ መርገም ፍቅር ቢሰጥሽ አትገኝም ወይ?

በየ ገዳሙ በየ አድባራቱ ፣
በመንበሩ ፊት የእምባየን ዛላ ሰውቸ ነበር
ባክሽ ወስኝ፣
"ያንተ ነኝ" በይኝ መባየ ይስመር!

ይህ አልሆን ብሎ...
የከፋሽ እንደሁ
የጨከንሽ እንደሁ ካላንቺ ላያምር የነፍሴ ነገር
አንድም ለእጣችን ኮከብ ላስቆጥር
አንድም ላስደግም ጠልሰመ ፍቅር
በየ ደብተራው መዞሬም አይቀር

(ታደሰ ደምሴ)
እዝጎ

#ሼርርር


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19