🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አንቺን እንዲሰጠኝ - ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ፤ ጧፍ መባ ገዛሁ - ልሰጠው ከሰማኝ፡፡ አንቺዬ... | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንቺን እንዲሰጠኝ - ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ፤
ጧፍ መባ ገዛሁ - ልሰጠው ከሰማኝ፡፡

አንቺዬ...
ፀሎቴን ሳልጨርስ - ብትይ እመጣለሁ፤
እኔ እኮ ሞኝ ነኝ፣
ፈጣሪዬን ትቼ - እጠብቅሻለሁ፡፡
እጠብቅሻለሁ!!!

በተገተርኩበት፤
እጠብቅሻለሁ፤
በተፈጠረኩበት፡፡

ጊዜ አይፈራረቅ - አይጮኹም አእዋፍ፤
አንቺን ስጠብቅሽ...
ለኮስኩት ጨክኜ - ለስለት እንዲሆን የገዛሁት ጧፍ፡፡

ትመጫለሽ አይደል?

(ኤልያስ ሽታሁን)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19