Get Mystery Box with random crypto!

ከታፈንኩ ኋላ ድፍን ሀገር ታሞ ፣ ሀኪም ሲቸግረው 'መድሀኒቴ አንቺ ነሽ' ፥ ስል ማንጎራጉረው አን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከታፈንኩ ኋላ
ድፍን ሀገር ታሞ ፣ ሀኪም ሲቸግረው
"መድሀኒቴ አንቺ ነሽ" ፥ ስል ማንጎራጉረው
አንዴ ላስነጠሰሽ
ይማርሽ እያልኩኝ ፣ ስጨነቅ የማድረው
ሀገር እያነባ
ስላንቺ ሳቅ ቅኔ ፣ የምደረድረው
ለምን ይመስልሻል?
።።።
ከታፈንኩ ኋላ...
የማይ የምሰማው ፣ እየሰቀጠጠኝ
ዛቻው እንደ በሶ ፣ እየበጠበጠኝ
እንደ ባህር ሞገድ ፣ ፍርሀት እየናጠኝ
ዝምታን መርጬ ፣ ጨለማ ሲውጠኝ
"ጀግና " ያለኝ ሁላ
"ፈሪ አረጉት" ብሎ ፣ ውብ ስሜን ሲያጎድፈው
ጊዜ እንደ ምዕራብ
ሀገሩን በሙሉ ፣ ፅልመት ሲያስታቅፈው
"ዐይኖቿ እንደኮከብ
ያበራሉ " የሚል ፣ ግጥም የምፅፈው
ለምን ይመስልሻል?
።።።
ከታፈንኩ ኋላ
ሲቃና መከራ
ደም እና ደንባራ
መቼም የማይለቃት ፣ አንድ ሀገር መውደዴን
የሚያውቁ በሙሉ ፣ ሳያውቁልኝ ጉዴን
"ዝመት እንጂ" ሲሉኝ ፣ ከፍቶኝ ማኮርፈው
ለምን ይመስልሻል
ስጋዬና ነፍሴን ፣ መንፈሴን ሚቀፈው?
.
.
.
.
ከአንቺ ርቄ ብዘምት
እኔም ሀገሬም ነን ፣ የምንሸነፈው ።

Belay bekle weya

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19