Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሄም በ ኤልሳ ክፍል 1 ቀኑ እየመሻሸ ነው እነ ዮናስም ቀጠሯቸውን ጠብቀው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 1


ቀኑ እየመሻሸ ነው እነ ዮናስም ቀጠሯቸውን ጠብቀው ለመገኘት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል ። ዮናስ ጓደኞቹን በሙሉ ጠርቷል ህሊናም እንደዛው ሴት ጓደኞቿን ለ እራት ግብዣው እያዘጋጀች ነው የዛሬውን ምሽት ለየት የሚያደርገው ከሁሉም ጥንዶች በላይ በጣም የሚያከብሩት እና የሚፈሩት ናሆም መኖሩ ነው ናሆም ሲበዛ ቆንጆ እና ይህ ቀረህ የማይባል ወንዳወንድ ነው ከሁሉም በ ኢኮኖሚ የሚበልጥና ግትር አቋም ያለው ስለሆነ ከሱጋር መሳፈጥ እንደ ትልቅ ድፍረት ይቆጠራል ....ህሊናም የ ናሆምን መምጣት ስላወቀች ጥንድነታቸው እንዳይጎድል በልመና ቤተልሄምን እንድትሄድ እየገፋፋቻት ነው
"ቤቲዬ በናትሽ ምን ችግር አለው ብዙም አንቆይም እኮ ደግሞ ፕሮግራሙን ትወጅዋለሽ እርግጠኛ ነኝ"
" ውይይይይ... ህሉ ለምን አተይኝም እኔ እናንተ ስቴዱ የምትለብሱት አለባበስ ምናምን አይመስጠኝም ዝምብላችሁ ሂዱ እኔ እዚሁ ፈታ እላለሁ!"
"ችግር የለውም የፈለግሽውን ልብስ አድርጊ ብቻ መሄዳችን ነው ዋናው እኛም ኮ ያላንቺ ይደብረናል ቤቲዬ! "
"እሺ በቃ እንደዛ ከሆነ ፒስ!....."

ቤቲ የሀብታም ልጅ ናት ነገር ግን በህይወት ያለችው አያቷ ብቻ ስለነበሩ በሌሎቹ ምክንያት ትጠጣ ነበር እጅግ በጣም የተጎዳች እና ውሎና አዳሯ ከሰፈሯ ዱርዬዎች ጋር የሆነ ለአይን የምታሳሳ ቆንጅዬ ልጅ ናት ። ጓደኞቿ ከሁሉም ለማንም አልገዛም የሚል ባህሪዋን ይወዱላታል ሲበዛ ደፋር እና ግትር ናት .....

የእራት ቀጠሮው ሰአት ደረሰ 4ቱም ሴቶች (ሰላም ፣ ሩት ፣ ህሊና ፣ ቤቲ ) እንደዚሁም 4ቱም ወንዶች (ፍፁም ፣ ልዑል ፣ ዮናስ እና ናሆም) ወደ ቀጠሮው ቦታ እያመሩ ነው።
እነ ዮናስ ቀድመው ገብተው ቦታ ይዘዋል ጥቂት ቆይተው እነ ህሊና ወደ ባለ 5 ኮኮቡ ሆቴል ገቡ............

ሁሉም በጣም አምሮባቸው ነበር ውድ የ እራት ቀሚሶችን ከ ኮስሞቲክሶች ጋር ለብሰዋል መጨረሻም አንድ ቆንጅዬ ልጅ ስልክ እያናገረች ተከትላቸው ገባች የተቦጨቀ ሱሪ ከ ባለኮፍያ ሹራብ እና ሰደርያ ጋር አድርጋለች ፀጉሯ ከግምባሯ ከፍ ብሎ ተይዞ ግማሹ ፍሪዝ ወደፊት ተንጠልጥሎ አይኖቿን ላሳይ አላሳይ ይላል!.
ለሌሎቹ ፀባዩዋ ስለሚታወቅ ምንም አልመሰላቸውም ናሆም ግን በጣም ተገርሞባት ነበር ከጓደኞቿ ካለመመሳሰሏም በላይ ከነሱ በኮስሞቲክስ ያጌጠ መልክ ይልቅ የሷ ያልተጠበቀ ውበት ልብ የሚያስደነግጥ መሆኑ አስገርሞታል ቢሆንም ምንም እንዳልመሰለው መስሎ ቀጥሏል ሁሉም ሰላም ተባብለው ተቀመጡ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲቀመጡ ጥንድ ያልነበሩት ናሆም እና ቤቲ ነበሩ ፊት ለፊት መፋጠጥ ጀመሩ ሁሉም የየራሱን ወሬ ይዟል ቤቲም ስልኳን መነካካት ጀምራለች ክብ ሰርተው በተቀመጡበት አስተናጋጇ መጥታ ታዘዘቻቸው እና የየራሳቸውን አዘው ከበሉ ቦሀላ መጠጣት ተጀመረ ብዙ መጠጦች በ ቦትል ቀርበዋል ወዲያው ቤተልሄም ስልክ ላይ አንድ መልእክት በ ቴሌግራም ገባ ልዑል ነበር ስለ ወንድምሽ አስገዳይ አንድ አንድ መረጃ ደርሶኛል በቅርቡ አጣርቼ እልክልሻለሁ ይላል አይታው የሚያስፈራ ፈገግታ ፈገግ ካለች ቦሀላ መጠጧን ተጎንጭታ ቀና ብላ ማየት ጀመረች ሁሉም ጥንዶች እያወሩ ነበር ድንገትም እያየች አይኖቿ ከ ናሆም አይኖች ጋር ተጋጩ ብዙም አልደነገጠችም እንደውም ምንም አልመሰላትም ስልኳን መነካካቷን ቀጠለች ቤቱ ውስጥ በተከፈተው ለስለስ ያለ ሙዚቃ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው መደነስ ጀመሩ በዚህ አጋጣሚ እነ ናሆም ወምበር ጋርም ሁሉም ተነስተው ቤቲ እና ናሆም ብቻ ቀሩ እንዳጋጣሚ ሁለቱም በ እኩል ሰአት አይኖቻቸው ተጋጩ ናሆም ተነስቶ የ እንደንስ አይነት ግብዣ አንድ እጁን ወደኋላ አንድ እጁን ደግሞ ወደ እሷ ዘርግቶ አቀረበላት
እስካሁን ቀና ብላ አላየችውም እነ ህሉ የናሆምን ሁኔታ አይተው በጣም ተገርመዋል ዳንሳቸውን አቁመው ሰፍ ብለው ያያሉ ናሆም እነሱ ሲያውቁት ሴት በጣም የሚንቅ አተራማሽ እና ጢባራም ፍቅር የሚባል ነገር የማያውቀው የቆንጆ ኩራተኛ ነበር ቤቱ ቀና ብላ ካየችው ቦሀላ መልሳ ስልኳ ላይ ተተከለች ሁኔታዋ በጣም አበሳጨው እነ ህሉም በጣም ደነገጡ ከነሱ ቡድን ሲያወራ እንኳን ዝም የሚባልለት ልጅ በ ቤቲ ሲናቅ ሲያዩ... በጣም ሀብታም በዛው ልክ በጣም አደገኛ እንደሆነም ያውቃሉ በንዴት "ማን ስለሆንሽ ነው ቆይ አንቺ ከኔ ጋር የማትደንሺው ?" ከጎን ያለውን ወምበር ስቦ እየተቀመጠ
"አልገባኝም?"
"ማንም ሴት ንቃኝ አታውቅም !"
"ምናልባት ሴት የሚለው ቃል የማይገልፃቸው ፍጥረታት ጋር ስለምትውል ይሆናል"
" ምን ማለት ነው የገዛ ጓደኞችሽን እየሰደብሻቸው ነው?"
"እነሱ ያንተ ሳይሆኑ የራሳቸው ሰዎች ናቸው "
" ማን እንደሆንኩ ታውቂያለሽ? ማንንም ሴት መጣል የምችል ሰው ነኝ ! "
"ይሆናል ችግሩ እይታህ ላይ ነው እኔ ማንም ሴት አይደለሁም ! ላዝህ እንጂ ልታዘኝ አትችልም እኔን ማዘዝ የሚችለው ብቸኛ አካል የሰራኝ ብቻ ነው!"
" ማን ስለሆንሽ ነው አንቺ እኔን የምታዢኝ ?"
" ቤተልሔም!" ብላ በተቀመጠበት ጥላው ወጣች በሁኔታው የደነገጠው ዮናስ ናሆም ጋር ሄደ
"ምንድነው?" አለው ናሆም ስሜቱን ለመፈተሽ በሚመስል አስተያየት እያየ
" ማናት? " አለው ስትወጣ በግምባሩ እያያት
" ቤቲ ናታ የ ህሉ የቅርብ ጓደኛ ናት!"
" ጥሩ በ 2 ቀን ውስጥ ስለሷ ሙሉ መረጃ እፈልጋለሁ !" ብሎ የተቀዳውን መጠጥ ባንድ ትንፋሽ ግጥም አድርጎ ጠጣው •••••••.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19