Get Mystery Box with random crypto!

''''ንገሯት ለእናቴ'''' ልጄ ልጄ ስትል ስሜን ስታዎሳ፣ ልሂድ አይኗን ልየው..... ልጠይቃት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

""""ንገሯት ለእናቴ""""

ልጄ ልጄ ስትል ስሜን ስታዎሳ፣
ልሂድ አይኗን ልየው.....
ልጠይቃት ብላ እግሯን ስታነሳ፣

እዳትመጪ በሏት ብትላችሁ እሽ፣
ልጅሽን ለማዬት እግርሽን አታንሽ፣
በቁሟ ሙታለች ብትችይ አታስታውሻት፣
ከነመፈጠሯ ከመኖሯም እርሻት፣

በሏት.....
አደራ ንገሯት አጥብቃችሁ ሞቴን፣
ብትናፍቀኝም.....
ላያታ አልፈልግም እንዲህ ሆኜ እናቴን፣

ወይም እዲህ በሏት ብላለች አትምጪ፣
ልጅሽ ክዳሻለች በቃ እርምሽን አውጪ፣
ወልደሽ አሳድገሽ ልጦርሽ ሲገባ፣
እናቷን ከሀዲ ሆነች የማትረባ፣

በሉልኝ ብታምን፣
አልባሷ ቡትቶ  ስራዋ ምናምን፣
ይቅርና ለናቷ ያልሆነች ለነብሷ፣
እርኩስ.... የረከሰች.....
ለሁሉ ከፍ የሚል ወለቂ ቀሚሷ፣
እንኳንስ ሊኖሯት ልጆችና ትዳር፣
ቤት የላት መጠጊያ አዳሯ መንገድ ዳር፣

ንገሯት ለናቴ ኑሮዬን ትረዳ፣
አትሆንም ለዘመድ አጠቅምም ለባዳ፣
ድሮ የምታቂው በልጅነት አለም፣
ያ የሚያምረው መልኳ ገፅታዋ የለም፣
በውስጥሽ ያለውን የልጅነት ምስሏን፣
አጥፊ ተያት እርሻት አታስታውሻት እሷን፣
በሏት......

አይ.... አይ.... አትበሏት.....
ይቅር አትንገሯት እውነታውን ለእማ፣
የሚጨክን አንጀት ይህን እየሰማ፣
ጆሮ ዳባ የሚል አካል ስለሌላት፣
በቃ እደውም ተዋት፣
እሽ አትልም ትምጣ፣
ልቀበላት እና አይታኝ እርሟን ታውጣ።


ኤዶምገነት ፃፈችው
@Edom_Ge

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19