Get Mystery Box with random crypto!

(በእመ ብርሃን...) ====++++==== አንዲት ምስኪን ህጻን የመንገዱን መብራት ቋሚ ተደግፋ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

(በእመ ብርሃን...)
====++++====

አንዲት ምስኪን ህጻን
የመንገዱን መብራት ቋሚ ተደግፋ
ድካም ተጫጭኗት
ባልጸና ደረቷ ማስቲካ ሸክፋ
ተስፋ በቆረጡ ኩልትፍትፍ
ፊደላት ቃል እየሰደረች
" በእመ ብርሃን አባት
  አንዲት ፍሬ ግዛኝ "
   አትለፈኝ አለች ...

በአይኖቿ ገመድ
በአንደበቷ እስራት
በልጅነቷ ክር
በሴትነት ጅማት
መሐከል ጠፍንጋኝ
እንደምን ልለፋት ?

እያቀረቀረች...እያዘነበለች
አዛኝቱን ጠርታ
ፊጥኝ እያሰረች
ልለፍ ቢል እግሬ እንኳ..ህሊናየን በየት
ታሳልፈዋለች ?

ያለኝን ብሰጥሽ
ልታፈላስፊኝ
ገፍቼሽ ብባዝን
በጸጸት ልትቀስፊኝ
በመንገዴ ቆመሽ...አትለፈኝ አትበይ
አንቺው አትለፊኝ  !

#Da_kiyorna

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19