ደብሮኝ ነበር ። ትንሽ አእምሮ እክል የገጠመው ሁለት ብር ስጠኝ እያለ የሚለምን ። ሲያየኝ ደስ የሚለው ሶስት ቀን ካለየኝ ምነው ጠፋ ብሎ ተገርሞ የሚጠይቀኝ ። ኮስተር ብሎ በዘጠናዎቹ.... ኔሽን ጋዜጣ ላይ እነ አሌክሳንድሮቪች ፣ጤርጥዮስ-ከቫቲካን የፃፉትን ሙግቶች ። ስነምግባር እና የእግዛብሄር ሃሳብ (Moral value and the idea of God) ያብራራልኛል ።1913- 1960 ድረስ ስለኖረው አልበርት ካሙ ስለ ሃሳብ ነፃነት ገደብ ሊጣልበት እንደማይገባ የተከራከረውን ። ቦንቦሊኖ እንዴት እንደተወደደ ...ጋዴ የሚሉት ጫማ ስለመጥፋቱ ስለማይወደው Nihilist ቱ ኒቼ ..... ለራሱ mental breakdown የገጠመው ሰውዬ እግዜር የለም አለ እያለ.... ሂሂሂሂ እያለ እየሳቀ ያጣጥልልኛል። ገሬ ቺክ ይፈራል ። አንድ ቀን "ሴክስ አድርገህ ታቃለህ እንዴ?" አልኩት እንዴት እንደተሽኮረመመ እንደ አስራ ሶስት አመት ልጅ አይነት መሽኮርምም ፊቱ ላይ ረበበ ። ስለ Sex እና Art ግንኙነት ስለሚዘበዝበው Eroticism and Aesthetics እያብራራ ....ወሲብ አድርገህ ታውቃለህ ስለው በዚህ መጠን መሽኮረመሙ ይገርመኛል የሆነ ሰሞን ድብርት ክፉኛ እየተላፋኝ ነበር ። ከማንም ጋ የማውራት አምሮት አልነበረኝም። የማውቀው ሰው ሲመጣ ችላ አለኝ እንዳይለኝ መንገድ የምቀይርበት ሰሞን ነበር ። የሆነ ቀን ማኪያቶ የምንጠጣበት ጥግ ጠርዝ ላይ ተቀምጬ መጣ ። ደና ነህ ገሬ አልኩት እጁን ላከልኝ ሲጨብጥ እጁን ላላ አደርጎ ነው " ጠፋህ እኮ? "አለኝ ። "አለው" ብዬው የሆነ ቀን እንደድሮ ሳንቀራረብ እሰጠው እንደነበረው አስር ብር ሰጠሁት ። አየኝ ብሩን አየው ተቀበለኝ ። ሄደ ። በነጋታው እመንገድ በጠዋት አገኘሁት ። ሲያየኝ ፈገግ ፈገግ አላለም ። ቀጥታ መጥቶ ..... "ራከኝ እኮ አስቀየምኩ እንዴ ማታ ሳስብ.. ሳስብ .. ሳስብ ... ሳስብ ነበር ። ሌላ እኮ እንዳንተ የሚያዳምጠኝ ማንም የለም ። ጓደኛዬ እኮ አንተ ብቻ ነህ" አለኝ ። አወራሩ ....ታረቀኝ ። እንደድሮ ጆሮ ስጠኝ ...ብር ሰጥተ አታባረኝ ....ነው እምለው ሳጣ" እ... አሞኝ ነበር" አልኩት ጓደኛ አመመኝ ተብሎ ይዘጋል ?? ይቅርታ ገሬ .... አየህ ገረመው እንደሆነ ስሜ አንተ ነህ የምታስታውሰኝ እኮ" ። .....ድንግጥ ብሎ "አሁን ተሻለ ግን ? " በኛ መሳቅ ውስጥ የሚስቁ ሲጎልብን የሚጎልባቸው ሰዎች ካሉን ብቻውን ቀላል አይደለም መሰለኝ!! Adhanom Mitiku ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 6.0K viewsAbela, 17:06