🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

እሱና እሷ እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣ ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣ ተፈቃቅረው ከርመው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እሱና እሷ

እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣
ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣
ተፈቃቅረው ከርመው ዓመታትን ቆጥረው፣
ጎጆ ለመቀለስ በአንድ ለመጠቅለል ሽማግሌ ልከው፣
ህይወት በአዲስ መልኩ ተጀመረ ይኸው።

የአንድ ቀን እይታ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ፣
ሙሽሪት ፀንሳ ቤተሰብ መስርቶ፣
ሁለትነት ቀርቶ በዝተው ተበራክተው፣
ዘር የሚያስቀጥል አዲስ ትውልድ ፈጥረው፣
ባል አክብሮ ሚስቱን ሚስት ለባል ተገዝታ፣
ፍቅርና መቻቻል በእነሱ ላይ ታይታ፣
ለማየት በቅተናል ፍቅራቸው አፍርታ።

በሳምሪ የዝኑ ልጅ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19