🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ
ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ
ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ
ፍፁም አንዳልጓጓ ህመም በርትቶብኝ
ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሞቴን ሲጠባበቅ
ህመሜን ሳዳምጥ ስሜቶቼን ሳረቅ
.
.
.
         መኖር ማለት ስቃይ
         መኖር ምለት ህመም
         መኖር ማለት ጭንቀት
         መኖር ማለት ድካም....

ወደ ተስፋ መንደር እልፍ ጊዜ ባመራ
የ እድሌን ልሻማ ከ እኩዮቼ ጋራ
ብፈልግ... ብጠብቅ ድርሻ የለኝ ሁኖ
ጠብታ እንኳን ሳይቀር ከ እኔነቴ ተኖ
ፀሐይ የለኝ ሁና ሕይዎቴ ዳምኖ
.
.
.
       ትላንት በመኖሬ ተስፋ እንኳን ሳይኖረኝ
       ምንም ያህል ባዝን የሚያልፍ ባይመስለኝ
       ቀን እየቆጠረ ቀን እየጨመረ
       የደመናው ጥቁረት መጠኑ ቀንሶ
       የስቃይ ዉርጅብኝ ከነበረው አንሶ
       ከ ሕይወቴ ጠፋ ቀስ በቀስ ጨርሶ...
.
.
.
የ ፀሐይ ዉበቷ
የፀሐይ ድምቀቷ
የዉበት ፍካቷ
ዛሬ ላይ ብሸፈን
ደመናው ሲገፈፍ ወደጎን ሲበተን....
.
.
.
       ህመም ብርድ ሁኖ ያገረጣው ትናንት
       ተንፏቆ እየዳሀ ዛሬን በመጠጋት
       አንድ ቀን ልጨምር ብዬ በመኖሬ
       ተስፋ ፀሐይ ሁኖ ከች አለልኝ ዛሬ!!
           
           ሚያዚያ 25 - 2016
                ዘይድ ሁሴን

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19