Get Mystery Box with random crypto!

የዛን እለት ማታ፣ ከንፈርሽን ስስም፣ የተሰማኝ ደስታ፣ መግለጽ ሁሉ አልችልም፣ በቃላት ጋጋታ፣ ብቻ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የዛን እለት ማታ፣
ከንፈርሽን ስስም፣
የተሰማኝ ደስታ፣
መግለጽ ሁሉ አልችልም፣
በቃላት ጋጋታ፣
ብቻ አልረሳዉም፣
የልቤን ትርታ፣
እና
የሳምኩሽን ቦታ፡፡

በቀኝ እጀ አዉሮፓን፣
በግራየ አፍሪቃን፣
የያዝኩ እስኪመስለኝ፣
በእልፍ አእላፍ ደስታ፣
ሲያራጀኝ ሲያቃጀኝ፣
የዛን እለት ማታ፣
ስስምሽ ከንፈርሽን፣
ጨረቃዋ በርታ፣
ባላሰብኩት ቅጽበት፣
አለሜ ሲሞላ፣
በገሀድ አየሁት፣
ፍቅርሽን ቀመስኩት፣
ከንፈርሽን መጠጥኩት፡፡

የዛን እለት ማታ፣
ከወሬ ያለፈ፣
ማያዉቀዉ ከንፈሬ፣
ከዉብ ከንፈሮችሽ፣
ሳቀርበዉ ደፍሬ፣
ያ ያንቀጠቀጠኝ፣
ብርዱ ከኔ ራቀ፣
መላ አካሌ ሞቀ፣
ፍቅራችን ደመቀ፡፡

የዛን እለት ማታ፣
በቅዱስዋ ምሽት፣
አምላኬን ለመንኩት፣
በግልጽ ባይገባኝም፣
ምን እንደጠየኩት፣
ብቻ ተዐምር ፈጥሮ፣
ሳይጎዳ ማንንም፣
አንቺን የኔ አድርጎሽ፣
ከህመሜ እንዳገግም፡፡

እንደዛ እለት ማታ፣
ከንፈርሽን ስስም፣
ጉንጮችሽን ስስም፣
ግንባርሽን ስስም፣
አንገትሽን ስስም፣
የኔ ብቻ ሆነሽ፣
እንድንኖር ዘላለም


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19