🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማስታወቂያ 1. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል በህግ የተቋቋመበትን 1ኛ | Beza International Church

ማስታወቂያ

1. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል በህግ የተቋቋመበትን 1ኛ አመት ምስረታን አስመልክቶ መጋቢት 5 ቀን፣ ማለትም የፊታችን እሁድ፣ በአ.አ ስታዲየም የምስጋናና የጸሎት ፕሮግራም የተዘጋጀ በመሆኑ፣ የሚቀጥለው እሁድ እዚህ ፕሮግራም አይኖርም። ከታች በተገለጹት ቦታውች ተግናኝተን አብረን ወደ ስታድየም እንጓዛለን።
• ሜክሲኮ ሸበሌ ፊትለፊት
• ቦሌ ደምበል ፊት ለፊት
• ፒያሳ ፖስታቤት ፊት ለ ፊት
• ባምቢስ ወረድ ብሎ መካነ እየሱስ ዋና ጽ/ቤት

2. ‘ያልተለመደ ፀሎት’ በሚል ለሃገራችንና ለሌሎች ጉዳዮች የምንፀልይበትን የፀሎት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። በአዲሱ ሕንፃ ታችኛው ፓርኪንግ በሚገኘው ትልቁ አዳራሽ ከፊታችን ሐሙስ የካቲት 11 ጀምሮ ይጀመራል።

ያልተለመደ ፀሎት ፕሮግራም
• ሐሙስ - ክቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት
• ዓርብ - ከጠዋቱ 1 ሰዓት - 4 ሰዓት
• ዓርብ - ከቀኑ 6 ሰዓት - 8:30 ሰዓት
• ዓርብ - ከቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት (የእንግሊዘኛ ፕሮግራም)
• እሁድ - ከጠዋቱ 1 ሰዓት – 2 ሰዓት

3. የልጆች ቤተክርስቲያን ስለተጀመረ አሁንም በጉባኤው ከ6-11 ዓመት ያሉ ልጆች ካሉ ወደ ክፍላቸው መሄድ ይችላሉ። ልጆች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ የሚሄዱት ቀጥታ ወደ ክፍሎቻቸው ነው።

4. የወጣቶች ቤተክርስቲያን ሊከፈት ነው። የእንግሊዝኛ ወጣቶች ቤተክርስቲያን መከፈቻ ዓርብ ከየካቲት 26 ቀን ከ12 ሰዓት ጀምሮ በቲኬ 8 ኛ ፎቅ ላይ ሲሆን የአማርኛ ወጣቶች ደግሞ በአዲሱ ህንፃ ምድር ቤት ውስጥ እሁድ ከየካቲት 28 ቀን ከ2:30 ሰዓት ጀምሮ ይሆናሉ። ልጆችዎን ይላኩ፤ ወጣቶች ተዘጋጁ!