🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የታሪክ የመጀመሪያ ገጽ!       የየካቲት 30/2013 ዕለታዊ ቃል ዘፍጥረት 15: 1-6ን  | Beza International Church

የታሪክ የመጀመሪያ ገጽ!
     


የየካቲት 30/2013 ዕለታዊ ቃል

ዘፍጥረት 15: 1-6ን አንብቡ



አዲሱን ጫማ በ60 የአሜሪካ ዶላር መግዛት እየቻላችሁ ጥቅም የዋለ ተራ ጫማ በ190,373 የአሜሪካ ዶላር ትገዛላችሁ? አንድ ሰው ግን ይህን አድርጎታል። ለምን? ይህ ስለጫማው ሳይሆን በጫማው ስለተደረገው ነገር ነበር። ጫማውን ማይክል ጆርዳን በ1984 በነበረው የኦሎምፒክ ጨዋታ የተጠቀመበት ጫማ ነው። በዚያ አሜሪካ ስፔንን 96 ለ 65 ባሸነፈችበትና የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በሆነችበት ግጥሚያ ማይክል ጆርዳን ይህን የ60 ዶላር ጫማ ተጫምቶ 20 ነጥብ አስቆጥሮ ነበር።
 
በዘፍጥረት 15 ላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጅ ቃል ገብቷል። እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ የተለየ ነገር አለመሆኑን ለመቀበል ትንሽ ጊዜ መውሰድ እንችላለን? ይህ የባህር መከፈል ወይም ተራሮች መፍለስ አልነበረም። አብርሃም ልጅ ለመውለድ ብቻ የተስፋ ቃል ፈለገ! አብርሃም ሌሎች ሁሉ እንደ ቀላል ነገር በወሰዱት የተስፋ ቃል ላይ እምነት ሊያሳድር ይገባ ነበር። አብርሃም አንድ ልጅ ለማግኘት ጉጉ ሆኖ ሳለ የአብረሃም አገልጋዮች ልጅ መውለድን አላቆሙም። አብርሃም የሚሰማውን ተስፋ መቁረጥና መሳቀቅ መገመት ትችላላችሁ።
 
ግን ለምን? አንዳንድ ጊዜ “ተራ” የሚመስልን ነገር ለማግኘት በብዙ ነገር ውስጥ ማለፍ እንዳለብን ለምን ይሰማናል? ግን እንደ ተራ የምንቆጥረው ከተራነት ያለፈ ሊሆን ይችላልን? ከሳራ ማህፀን የሚወጣው ልጅ ብቻ ሳይሆን ህዝብም ነበር! እናም አብርሃምና ሣራ እንደዚህ ያሉ ከተለመደው ያለፉ መሰናክሎችን የገጠሙበት ምክንያት ጉዳዩ ከተራነት ያለፈ ተልእኮ ስለነበረ ነው። ግን የታሪኩን መጨረሻ የማወቁ ጥቅም እንዳለው መገንዘባችን ለእኛ ቀላል ነው።

"ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብርን ያስገኝልናል" 2 ቆሮንቶስ 4 17
 
በእኛ እና ቀደም ሲል በተጠቀሰው ገዢ መካከል ያለው ልዩነት ገዢው በተጠናቀቀ የታሪክ የመጨረሻ ገጽ ላይ የከፈለ መሆኑ ነው። ለተጠናቀቀ ታሪክ ዋጋውን ለመክፈል ፈቃደኛ ነበር። እግዚአብሔር ግን ባልተጠናቀቀ የታሪክ የመጀመሪያ ገጽ ላይ  እንድንከፍል እየጠየቀን ነው። እንድንከፍል የተጠየቅነው ገንዘብ በዶላር ሳይሆን በትእግስት፣ በእምነት እና በእምነት ነው። ስለዚህ፣ እግዚአብሄር በሰጠን የታሪክ ጅማሬ መጀመሪያ ገጽ ላይ ባለ ታሪክ(ተስፋ) እናምናለን? ወደሚለው ጥያቄ እንመጣለን። የምናምን ከሆነ ለታሪኩ(ለተስፋው) የምንከፍለውን ዋጋ ተገቢ/አሳማኝ ያደርገዋል።
 
የሕይወት ተዛምዶ
እግዚአብሔርን እንመን!

ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ የበለጠ እንድታመንብህ  ጸጋህን ስጠኝ።