🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

መንፈሳዊ እሳታችሁን እንዲቆይ አድርጉት! መጋቢት 2/2013 ዕለታዊ ቃል 1 ሳሙኤል 10፡ 9-1 | Beza International Church

መንፈሳዊ እሳታችሁን እንዲቆይ አድርጉት!


መጋቢት 2/2013 ዕለታዊ ቃል
1 ሳሙኤል 10፡ 9-1፣ ሮሜ 12፡ 2ን አንብቡ



አዲአርሶ አደሩ በአንድ ወቅት በድርቅ ወቅት መጠቀም የሚያስችለውን የዝናብ ውሃ የሚያጠራቅምበትና ይሚያቆይበት አሰራር ነበረው። የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ገንብተው የዝናቡን ውሃ ይሰበስቡና ያጠራቅሙ ነበር። ስለዚህ ጥያቄው ዝናብ በወቅቱ መኖሩ ብቻ ሳይሆን አርሶ አደሩ ምን ያህሉን የዝናብ ውሃ አቆይቶታል? የሚለው ነው።

ሳውል ስለራሱ ስራ ብቻ የሚያስብ ተራ ሰው ነበር፤ እናም ይህ ከመለኮት ጋር መገናኘቱና መነካካቱ ሕይወቱን ከመሰረቱ ለወጠው። እሱ ንጉሥ መሆን በጭራሽ አስቦ አያውቅም። ነገር ግን በሆነ መንገድ እርሱ በትንቢታዊ እጣ ፈንታው ላይ አረፈ። እግዚአብሔር ልቡን ቀየረ። እርሱ ካሁን በፊት ሆኖ በማያውቀው ሁኔታ ተሰማው፤ አሰበ፤ ፈለገ፤ እናም ተናገረ። ግን የሳኦልን የሕይወት ፍፃሜ ስናይ በዕለት ተዕለት ሕይወቱ ያንን ሁሉ መንፈሳዊ ልምምድ ማቆየት እንዳልቻለ እናያለን።

ሮሜ 12፡1 በመለወጥ ሂደት እንድንቀጥል ይነግረናል። በአይምሯችን መታደስ መለወጥ እንጂ ይህን አለም እንዳንመስል ይነግረናል።

ከመለኮት ጋር መገናኘትና ትንቢታዊ ቃል ማውጣት፤ አስደናቂ ተስፋን ከጌታ መቀበል ታላቅ ነገር ነው። በመንፈስ መውደቅ/መባረክ እና ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ ግንኑነቶችን ማድረግ ድንቅ ነገር ነው። ነገር ግን እንደ አማኝ ይህንን መንፈሳዊ እሳት ግለቱ ሳይበርድ እንዴት ማቆየት እንደምንችልና በመለወጥና በማደግ መቀጠል የምንችልበትን ሁኔታ መማር አለብን። በኮንፈረንስ ወይም በእሑድ አገልግሎት ከሚሆነው በላይ፣ በየቀኑ የምንመገበው ቃሉ እና ከእርሱ ጋር የሚኖረን ቀጣይነት ያለው ህብረት ነው መንፈሳዊ እሳቱን የሚያቆይልን። ስለዚህ ከጌታ ጋር ባለን ህብረት እንድናድግ የሚረዱንን የዕለት ተዕለት ህብረት፤ ጸሎት፤ አምልኮ፤ እና የቃል ጥናት ልምድ ማዳበር አለብን። የእግዚአብሔር ቃል እውነት አስተሳሰባችንን እና ባህሪያችንን በየቀኑ እንዲያድስ መፍቀድ አለብን።

የሕይወት ተዛምዶ
ከጌታ ኢየሱስ ጋር ህብረት የምታደርጉበትና ይህን ልምድ የምታዳብሩበት በቀን ውስጥ የተወሰነ ጊዜ መድቡ።

ፀሎት
ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ አንተን መምሰል እፈልጋለሁ። ቃልህንና ጸጋህን በህይወቴ ማቆየት እንድችልና በዘላቂነት አንተን እየመሰልኩ እንዳድግ እባክህ እርዳኝ። አሜን!