🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ፍሬያማ ሁን! መጋቢት 3/2013 ዕለታዊ ቃል ቆላስያስ 1: 10ን አንብቡ የሰውን ልጅ ዘ | Beza International Church

ፍሬያማ ሁን!


መጋቢት 3/2013 ዕለታዊ ቃል

ቆላስያስ 1: 10ን አንብቡ



የሰውን ልጅ ዘፍጥረት ስናጠና ሰው ከእግዚአብሔር የሰማው የመጀመሪያው ነገር ፍሬያማ ሁን የሚል እንደነበረ እናገኛለን። በሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ፍሬያማነት ለተለያዩ ልኬቶች ብዙ ጊዜ እንደተጠቀሰ እናገኛለን። ሆኖም፣ ህይወታችን በውስጡ በርካታ ንብርብሮች ያሉት በመሆኑ፣ ፍሬያማነት ለእያንዳንዳቸው ተገቢ ሊሆን ይችላል።

እንደ አማኞች ሁላችንም በተሰጠን እንጀምራለን። የእግዚአብሔር ቃል ሁላችንም እኩል እንደጀመርን ወይም ተመሳሳይ አቅም እንዳለን አይነግረንም። ሆኖም ፈጣሪያችን ከሁላችን ፍሬያማነትን እንደሚጠብቅ በግልፅ ያሳያል።
 
ኢየሱስ  “ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡት በዚህ አባቴ ይከብራል” ብሏል። ዮሐ 15: 8 ተፈጥሮን በመመልከት ፍሬያማነት በቀላሉ እንደማይመጣ መረዳት እንችላለን። ሞግዚቱ በትክክል መንከባከብ ይኖርበታል። የምሳሌ መጽሐፍ ጥሩ ተንከባካቢ ባላደራነት በሌለበት ሁኔታ ስለሚሆነው ነገር ጥሩ ሥዕል ይሰጣል፤ “በሰነፍ ሰው እርሻ በኩል አለፍሁ፣ ማስተዋል የጎደለውን ሰው የወይን እርሻ አልፌ ሄድሁ፣ በያለበት እሾህ በቅሎበታል፣ መሬቱም አረም ለብሷል፣ ቅጥሩም ፈርሷል። ” ምሳሌ 24:30 በተመሣሣይ ሁኔታ በሕይወታችን ውስጥ ያለው ተቀማጭ ፍሬያማ እንዲሆን  መንከባከብ አለበት። አእምሯችን ለጌታ ባልተማረከ ጊዜ ጠላት ከፍሬያማነት የሚያርቁን ብዙ ሀሳቦችን ይዘራበታል።

በዘፍጥረት 49 22 ላይ “ዮሴፍ ፍሬያማ የወይን ተክል ነው፣ በምንጭ ዳር የተተከለ  የወይን ተክል ነው፣ ሐረጎቹ  ቅጥርን  ያለብሳሉ።” ይላል።
 
ሕይወቱን ስንመረምር ፍሬ አልባነትን እንዴት እንደሸሸ ማየት እንችላለን። የእሱ ሕይወት የቤተሰብ ውሳኔ ተጠቂም የሆነ፤የአለቆች ውሳኔ ተጠቂ የሆነ ይመስላል። እሱ በዝምታ ውስጥ እየተንከባለለ እና በድብርት ለመኖር እራሱን መፍቀድ ይችል ነበር። ዛሬ ቢሆን ኖሮ ራሱን በራሱ ቢያጠፋ እንኳንባልተገረምን ነበር  ሆኖም ዮሴፍ ከጌታ ጋር መሆንን መረጠ እና ባለው  ነገር ሁሉ አገልግሏል።

አመለካከቱ ባለው ነገር የተቻለውን ሁሉ  መልካም ማድረግ እና እሱ ሊኖርባቸው ለሚችሉ ፍሬ አልባ ትዝታዎች እና እርግጠኛ ባልሆነባቸው ነገሮች ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር ላይ የታመነ እነደሆነ  አስባለሁ፤ሆነም ቀረም ከሁሉም  በአምላኩ የመጨረሻ ዕቅድ ወይም ጊዜ ላይ ግልጽነት አልነበረውም።
ዮሴፍ ቸልተኛ አልነበረም  መጽሐፍ ቅዱስ “ፍሬያማ እና ስኬታማ ሰው” ብሎ እንደጠራው ጥሩ ባላደራ ነበር።
 

የሕይወት ተዛምዶ
ፍሬያማ ከመሆን ያገደኝ ምንድነው?ስንፍና ነው? ጉዳት ነው? ድንቁርና? መንፈስ ቅዱስን ቸል እያልኩ ነው?

ፀሎት
ጌታ ሆይ በሕይወቴ ፍሬያማ እንድሆን እርዳኝ።