🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የአቤል መሥዋዕት ! መጋቢት 4/2013 ዕለታዊ ቃል ዘፍጥረት.4÷3-7 ን አንብቡ የዘፍጥ | Beza International Church

የአቤል መሥዋዕት !


መጋቢት 4/2013 ዕለታዊ ቃል

ዘፍጥረት.4÷3-7 ን አንብቡ



የዘፍጥረት መፅሐፍ የብዙ ነገሮች መጀመሪያ መፅሐፍ ሲሆን ከዚህም መካከል አንዱ ሰው ለእግዚአብሔር የመጀመሪያውን መሥዋዕት እንዳቀረበ ተዘግቦልናል። መሥዋዕት ማለት ለምናመልከው አምላክ ፍቅራችንን የምንገልፅበት እና የምናመሰግንበት መንገድ ነው።
 
"አቤል ከቃየል ይልቅየበለጠ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ" ዕብ.11÷4
 
የአዳምና የሔዋን የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ወንድማማቾች በእግዚአብሔር የሚያምኑ ነበሩ። ከዕለታት አንድ ቀን ለእግዚአብሔር ካላቸው ነገር መሥዋዕትን አቀረቡ እግዚአብሔር ግን ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ይላል። ግን ለምን አቤል ያቀረበው መሥዋዕት ከቃየል ይልቅ የሚበልጥ ተባለ? ወደ ቃየልስ መሥዋዕት ለምን ይሆን እግዚአብሔር ያልተመለከተው። እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ክፍሉን በአንክሮ መመልከት ተገቢ ነው። ፀሐፊው እዚህ ላይ በአቤልና በቃየን መካከል የተሰዋውን መሥዋዕት በማነፃፀር እያቀረበልን አይደለም። እንዲሁም እግዚአብሔር የአቤልን መሥዋዕት መቀበሉ እንስሳን ስላቀረበና፤ የቃየን መሥዋዕት ደግሞ ተቀባይነት ያላገኘው ከምድሪቱ ፍሬ የእህል መሥዋዕት ስላቀረበ አይደለም። ታዲያ በሁለቱ መሥዋዕት አቅራቢዎች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ምንድን ነው ስንል እግዚአብሔር በይበልጥ ያተኮረው መሥዋዕቱን ባቀረቡት ሰዎች የልብ ዝንባሌ ላይ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር መሥዋዕቱን ሳይሆን በመጀመሪያ የሚመለከተው አቅራቢውን ነው። በክፍሉ ላይ እንደምንመለከተው እግዚአብሔርም ወደ አቤልና… ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ነገር ግን ወደ ቃየንናወደ መሥዋዕቱ አልተመለከተም ይላል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍለጎት መሥዋዕታቸው ላይ ሳይሆን  እነርሱ ላይ ነበር። የአቤልን ልብ ሲመለከተው እምነት ያየበት ሲሆን በቃየል ልብ ግን ምናልባት ተቃራኒውን ይሆናል። ምክንያቱም የመስዋዕታቸው ውጤት ሁለቱንም ገለጣቸው አንዱ ገዳይ ሌላው ሟች ሆነ።

የዕብራውያን ፀሐፊ የአቤልንና ቃየንን መስዋዕት ያመጣውን ውጤት ገልጿል። የአቤል መሥዋዕት ብልጫ ያሳየበት ምክንያት በእምነት ማቅረቡ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት ፃድቅ እንደሆነ ተመሠከረለት።(ዕብ.11÷4)

ዛሬ ብዙ ዓይነት መሥዋዕት ሊቀርብ ይችላል ዋናው ግን እግዚአብሔር ሲመሰክርልን ነው። ከመሥዋዕታችን ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው የልባችን መሰዊያ ቅኝት ወሳኝ ነው። በቃየል ልብ ውስጥ የተደበቀ ማንነት መሥዋዕቱን ተከትሎ ወጣ። ለእግዚአብሔር ከምናቀርበው መሥዋዕትና ምሥጋና ይልቅ ወንድማማችነት ሕብረትና ወዳጅነት ይበልጣል። (ማቴ.5÷23-2)5 ከሚታዬው ከምንሰጠው ነገር የበለጠ፤ የማይታየው የምንሰጥበት የውስጣችን የልብ ተነሳስቶት እግዚአብሔርን ይስበዋል።  
 
የሕይወት ተዛምዶ
ከመሥሰዋታችንና ከመስጠታችን በፊት የልባችንን ዝንባሌ እንፈትሸው። እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና።
 
ፀሎት
እግዚአብሔር ሆይ ልቤን ተቆጣጠርልኝ።