🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በትህትና ወደፊት መራመድ የመጋቢት 9/2013 ዕለታዊ ቃል 1ኛ ሳሙኤል 25፡2-39ን አንብቡ | Beza International Church

በትህትና ወደፊት መራመድ

የመጋቢት 9/2013 ዕለታዊ ቃል
1ኛ ሳሙኤል 25፡2-39ን አንብቡ


እኛ ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ የትህትናን አቅም አቅልለን እናየዋለን። ከየትኛውም ነገር በላይ ሁኔታዎችን የማርገብ አቅም አለው።

በ 1 ሳሙኤል 25 ውስጥ ስለ አቢግያና ናባል ታሪክ እንማራለን። ናባል በሁሉም ድርጊቶቹ ውስጥ ጨካኝና ክፉ እንደነበረ ይናገራል። ናባል ዳዊትንና ሰዎቹን ዞር በሉ ብሎ የዳዊትን ጥያቄ እምቢ ባለበት ጊዜ ነገሮች ወደ መልካም አቅጣጫ እንደማይሄዱ ግልፅ ነበር፣ ነገር ግን አቢግያ ጣልቃ ለመግባት ወሰነች። በዚህ የአቢግያ ውሳኔ ላይ አስገራሚ የሆነው ነገር ባለቤቷ በእውነቱ ልትከላከልለት የማይገባ ሰው መሆኑ ነው። በራሱ ራስ ወዳድነት ምርጫውን አድርጓል ነገር ግን አቢግያ አሁንም በእርሱ ምትክ ጣልቃ ለመግባት ወሰነች። ባሏን ለመከላከልና በዳዊት ፊት ለመቅረብ የትህትናን መንገድ መረጠች።

ዳዊት አቢግያን ሲያገኛት ትህትናዋ ሁኔታውን ባንዴ አረገበው። በእውነቱ ዳዊት ናባልን ከመርገምና ቤተሰቡን ሁሉ ከማጥቃት ይልቅ በምትኩ አቢግያን ባረካት። የአቢግያ ትህትና የመላው ቤተሰቧን ፍርድ ወደ በረከት ተቀየረ።

በዛሬው ዓለም ትሑት የሆነውን መንገድ መውሰድ ብርቅ ነው። በራሳችን መረዳት ላይ ቆመን ትክክለኛ መሆንንና ሌሎችን መወንጀል እንመርጣለን። ሆኖም ከአቢግያ አንድ ነገር መማር አለብን፤ ብዙውን ጊዜ ትክክለኛ ከመሆንና ፍርድ ከመስጠት ይልቅ ላላጠፋነው ነገር ጥፋተኝነትን መቀበልና ትሁት መሆን የተሻለ ነው። በውጤቱ ልትገረሙ ትችላላችሁ። ቅጣት ይመጣል ብላችሁ ባሰባችሁበት በረከት ልትቀበሉ ትችላላችሁ።

ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተወውና በረከትን ለማምጣት በትህትና የሚራመዱ ሰዎች እንሁን።

የሕይወት ተዛምዶ
በአሁኑ ሰዓት የትህትናን ጎዳና ልትወስዱበት የምትችሉበት ሁኔታዎች አሉ?

ፀሎት
እግዚአብሔር ሆይ፣ ለስምህ ክብር ለማምጣት በትህትና የምንራመድባቸውን አጋጣሚዎች አሳየን።