🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ውድ ቤዛ ፣ ሁላችሁም እንደምታውቁት የኮቪድ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ነው። በዕለት ተዕለት ግንኙነ | Beza International Church

ውድ ቤዛ ፣

ሁላችሁም እንደምታውቁት የኮቪድ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ነው። በዕለት ተዕለት ግንኙነቶችዎ ጠንቃቃ እንዲሆኑና ሃላፊነት በተሞላው መንገድ እንዲንቀሳቀሱ እናበረታታዎታለን። ነገር ግን እርስዎ፣ የሆም ኬርዎ አባል ወይም ለእርስዎ ቅርብ የሆነ ማንኛውም ሰው በኮቪድ ምርመራ ፖዘቲቭ ከሆኑ እባካችሁ አሳውቁን።

በእነዚህ መንገዶች ያግኙን፦
• የሆም ኬር መሪዎን ያነጋግሩ
• በቴሌግራም @bezaconnect ላይ ይጻፉልን
• በኢሜል አድራሻ connect@bezainternational.org ላይ ይጻፉልን
• በ 0907700007 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን

በዚህም መሪዎች ያላችሁበትን ሁኔታ አውቀው እንዲጸልዩልዎት ያስችላቸዋል።

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ። (ኢሳይያስ 41:10)

ተባረኩ እናም ራሳችሁን ጠብቁ፣