🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማስታወቂያ የቤዛ ፆም ፀሎት:- እዚሁ ቤዛ ታበርናክል የፊታችን ረቡዕ ከግንቦት 24-26 ከጠዋቱ | Beza International Church

ማስታወቂያ

የቤዛ ፆም ፀሎት
:- እዚሁ ቤዛ ታበርናክል የፊታችን ረቡዕ ከግንቦት 24-26 ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መደበኛ የ3 ቀን የጾም ፀሎት ፕሮግራም ይኖረናል። እባካችሁ ቀኑን መዝግቡት እና የጌታን ፊት ለመፈለግ እንደ አካል እንሰባሰብ!

የፍቅርና የመፅናናት ህብረት /ዕድር/:-
• በዋናነት ዓላማው ቅዱሳንን በሃዘናቸው ጊዜ አብሮ ለመሆን።
• በቀጣይ ግን በየሰፈሩ ካለውየሆም ኬር አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ለመጎብኘትም የሚረዳ አግልግሎት ነው።
• ስብሰባ ግንቦት 27 በ 5፡00 ሰዓት በዚሁ በቤተክርስቲያን ይኖረናል።

የአምልኮ ምሽት:- የእንግሊዝኛው የአምልኮ ቡድን ሰኔ 1 ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ የአምልኮ ምሽት አዘጋጅቷል። አብረን ጌታን እናምልክ!

የአማርኛ ድራማ እና ጥበብ አገልግሎት:-ወንድማችን ኤፍሬም የአማርኛ ድራማ እና ሥነ ጥበብ አገልግሎት እየመራ ነው። ስለዚህ የዚያ አገልግሎት አካል መሆን ከፈለጋችሁ እባካችሁ በዚህ ቁጥር "0907700007" አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ "@bezaconnect" ይመዝገቡ።

የቤዛኪድዝ የህፃናት አገልግሎት:- እስካሁን ለአዲሱን የቤዛኪድዝ የህፃናት አገልግሎት ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች ከቤተሰብ ጋር የበለጠ ግንኙነት ለመፍጠር እንፈልጋለን። የልጆቻችን የወደፊት ተስፋ ብሩህ ነው!

ስለዚህ ልጆቻችሁን በዚህ ሊንክ እንድትመዘግቡ እንጠይቃችኋለን:: http://bit.ly/AmharicKidzRegistration

የቤዛ ሰንበት ትምህርት ቤት ምዝገባ:- ቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን ከ2 - 11 አመት ለሆኑ ህጻናት የሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት በመስጠት ደስተኛ ነች። አምስት ክፍሎች አሉን።

የአምልኮ ሰዓት:- የእሁድ የአምልኮ ሰዓት፦

የአማርኛ አገልግሎት፦ ከ2:45 - 4:45
የእንግሊዝኛ አገልግሎት፦ ከ5:15 - 7:15

የልጆች የሰንበት ትምህርት ፕሮግራም ፦

ዕድሜያቸው 2 እስከ 3 - ከአምልኮ በኋላ ወዲያውኑ ይጀምራል
ዕድሜያቸው 4 እስከ 11 - በ3:15 ሰዓት ይጀምራል
ዕድሜያቸው 12 እስከ 14 እድሜ - በ2፡45 ሰዓት ይጀምራል

የወጣቶች ፕሮግራም:- የቤዛ የወጣቶች ፕሮግራም ዕድሜያቸው ከ 15-23 ለሆኑ በየሳምንቱ እሁድ በአዲሱ ሕንጻ ቤዝመንት ከ 2፡45-4፡45 ይካሄዳል።

የደቀመዝሙርነት ትምህርት:- የደቀመዝሙርነት ትምህርት እሁድ በታበርናክል ከጠዋቱ 4፡45 እስከ 5፡45 ሰዓት ይካሄዳል። እሁድ መውሰድ የማይችል ማንም ሰው የደቀመዝሙርነት ትምህርት መውሰድ ከፈለገ በሌሎቹ ቀናት ፕሮግራም ስለምናዘጋጅ የምትፈልጉ እባካችሁ በዚህ ቁጥር "0907700007" አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ "@bezaconnect" ይመዝገቡ።

ያልተለመደ ፀሎት ላለፈው ወር በርትቶ እየቀጠለ ነው። በቤዛ ቤተክርስቲያን የተጀመረው የፀሎት እንቅስቃሴ በየሳምንቱ እየቀጠለ ስለሆነ ይምጡና ለሃገራችንና ለተለያዩ ጉዳዮች ማልዱ። በአዲሱ ህንፃ ምድር ቤት ለፀሎት በተዘጋጀው አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ ነው። ለኮቪድ የሚያስፈልጉት ጥንቃቄዎች ሁሉ በፀሎት ጊዜውም እየተከተልን ነው።
ያልተለመደ ፀሎት መርሃ-ግብር፦

ሐሙስ - ክቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት
ዓርብ - ከቀኑ 5:30 ሰዓት - 8:30 ሰዓት (የእህቶች ፕሮግራም)
ዓርብ - ከቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት (የእንግሊዘኛ ፕሮግራም)
ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰዓት-2 ሰዓት በዙም (ለመግባት ይህንን ኮድ ይጠቀሙ: 84216976202)
እሁድ - ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት – 2:30 ሰዓት

የአንድ ብሎኬት ለሕንፃው ፕሮጀክታችን ተጀምሯል፡፡ ከአሁድ ፕሮግራም ስትወጡ በ50 ብር ከተዘጋጁት ብሎኬቶች በመግዛት ራዕዩን ወደ ፍፃሜ እናምጣው፡፡