🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የመንገድ መዘጋት ማስታወቂያ Road closure announcement ነገ ለማምለክ ሲመጡ ለመከላ | Beza International Church

የመንገድ መዘጋት ማስታወቂያ Road closure announcement

ነገ ለማምለክ ሲመጡ ለመከላከያ ድጋፍ ሰልፍ ስለሚደረግ እነዚህ መንገዶች ዝግ ስለሚሆኑ አቅደው ይምጡ፡፡

As you come to worship tomorrow, please plan ahead as these roads will be closed due to the government program in Meskel Square.

እሁድ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ " በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል " በሚል መሪ ቃል ለፖሊስ አመራር እና አባላት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

ይህን ተከትሎ ስነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፦

➤ ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር (ኦሎፒያ አደባባይ)

➤ ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ በላይና በታች

➤ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ

➤ ከቸርችል ጎዳና በሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፖስታ ቤት

➤ ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

➤ ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

➤ ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና አካባቢ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር

➤ ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሜክሲኮ አደባባይ

➤ ከሚክሲኮ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር መብራት

➤ ከሰንጋ ተራ በቴሌ ባር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች በድሉ ህንፃ አካባቢ

➤ ከንግድ ማተሚያ ቤት በውስጥ ለውስጥ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦርማ ጋራዥ አካባቢ

➤ ከሸራተን ወደ አምባሳደር ለሚመጡ ፍል ውሃ አካባቢ

➤ ከካዛንቺስ በኩል ወደ ፍል ውሃ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10፡30 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል።