🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

 የሰኞ ጠዋት ንባብዎ ኢየሱስ እንባውን አፈሰሰ ዮሐንስ 11፡ 35 የዚህን ሳምንት መልእክት ያመ | Beza International Church

 የሰኞ ጠዋት ንባብዎ

ኢየሱስ እንባውን አፈሰሰ
ዮሐንስ 11፡ 35

የዚህን ሳምንት መልእክት ያመጣው ወንድማችን ኤድዋርድ ብራውን ነው።

ዮሐንስ 11፡ 35 ኢየሱስ እንዳለቀሰ ይነግረናል። ይህ ቃል በጣም ቀላል፤ ግን ደግሞ እኛ አዋቂዎች ለመረዳት የሚያስቸግረን ሚስጥራዊ ጥቅስ ነው።ኢየሱስ ማልቀሱ ሁለት ጊዜ በወንጌል ተዘግቧል፤ እናም ይኸኛው በጣም የግል ስሜቱ ነበር።

ኢየሱስ ለምን አለቀሰ?
ኢየሱስ አልዓዛርን እንደሚያስነሳው እያወቀ ያለቀሰው ለምንድን ነው? ለዚህ ሁለት ምክንያቶች አሉ። የመጀመሪያው ምክንያት ፍቅር ነው። ኢየሱስ ማርያምንና ማርታን ይወዳቸው ስለነበር እነሱ ሲያለቅሱ አይቶ አለቀሰ። ለቅሶ ይጋባል፤ በተለይ የምትወዱት ሰው ሲያለቅስ ብታዩት እናንተም ታለቅሳላችሁ። 
ነገር ግን ኢየሱስ እየመጣ ያለው ወደ ቀብር ሳይሆን ወደ ትንሣኤ ነበር። እርሱ ምን ሊያደርግ እንደሆነም ያውቅ ነበር። የእርሱ እቅድ ከኛ እቅድ የተሻለ ነው። እግዚአብሔር አይዘገይም።

ሁለተኛው ምክንያት ኢየሱስ ሞትን ስለሚጠላ ነው። ሞት የኃጢአትና ያለማመን ውጤት ነው። እርሱ ያፈሰሰው እንባ የንዴት የቁጣ እንባ ነበር። የእርሱ እንባ የሀዘን ብቻ ሳይሆን የቁጣም እንባ ጭምር ነው። እርሱ አልአዛርን ማስነሳት መቻሉን አለማመናቸውንና ሲያለቅሱ ማየቱ በውስጡ ጥልቅ ንዴትና ቁጣ አደረበት። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ሲናገር “ኢየሱስ መንፈሱ ታወከ” ይላል። (ዮሐንስ 11፡ 33) ይኸው ግስ በጌቴሰማኒ የአትክልት ስፍራና በቤተሳይዳም ጥቅም ላይ ውሏል።

በሕይወታችሁ በቁጣ  በንዴት እንባችሁን እያፈሰሳችሁ ያለቀሳችሁበትን አጋጣሚ አስቡ። ዓይናችሁን ጨፍኑና ምን ታስቡ እንደ ነበር፤ ምን አይታችሁና ምን ተሰምቷችሁ እንደ ነበር አስታውሱ። ይህን ትውስታ ልክ እንደ ወርቅ አጥብቃችሁ ያዙት፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እነዚህን ትውስታዎች ዛሬ ይጠቀምባቸዋል። ከፈቀዳችሁለት በቀሪ ሕይወታችሁ ይጠቀምባቸዋል። ጌታ ስለ እናንተ ይማልዳል። "ጠላት ለክፋት ያሰበውን እግዚአብሔር ለመልካም አደረገው" (ዘፍ 50: 20)። ኢየሱስ ፍፁም ሰው ስለሆነም ህመማችንና እንባችን ይገባዋል። እርሱ በመንፈስ ድሆች ለሆኑና ለተጨቆኑ ትኩረት ይሰጣል፤ አብሮም ያዝናል። ጠንካራና ብርቱ የሆኑ መሪዎች ሊያለቅሱ እንደሚችሉ መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ዳዊት ሞትን አልፈራውም፤ ግን ያለቅሳል። መግደላዊት ማሪያምና ሌሎቹም ኢየሱስን ለመከተል ብርቱ ነበሩ፤ ግን ደግሞ በእግሩ ስር ያለቅሱም ነበር።

ኢትዮጵያ እንደ አላዛር
እኔ ዛሬ ለኢትዮጵያ አንድ መልእክት አለኝ። ኢትዮጵያ እንደ አላዛር ነች። ወደ መገናኛ ብዙኃን ብትሄዱ
ዓለም ሁሉ የኢትዮጵያን የሞት ዜና መስማቱን እንደ ቀጠለ ነው። ግን ኢትዮጵያ በጣም ህያው ነች። እንደገናም ትነሳለች። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ዋና ከተማ ነች። ስለዚህም አፍሪካም ትነሳለች። እኛ ተስፋችን ተሟጦ መጠበቅ ስናቆም እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ሊያድነን  ይመጣል። ለእግዚአብሔር የማይቻል ነገር የለም። ኢትዮጵያ በመፅሃፍ ቅዱስ ከ 50 ጊዜ በላይ መጠቀሷ ለኔ ተስፋ የሚሰጠኝ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር እቅድ አካል ነች። እግዚአብሔር ቀጣይነት ያለው ዓላማ አምላክ ነው። እዚህ የጀመረውን እዚሁ ይጨርሰዋል።

የሀዘን እንባ አለ፤ ግን ደግሞ የደስታም እንባ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ መዝ 30: 5 “ሌሊቱን በለቅሶ ቢታደርም በማለዳ ደስታ ይመጣል” ይላል። ራዕ 21፡ 4 ላይ “እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሀዘን፣ ለቅሶ ወይም ስቃይ አይኖርም።” ይላል።  ዳዊትም መዝሙር 56: 8 ላይ “እግዚአብሔር የዳዊትን እንባ በእቃው እንደሚያጠራቅም በመዝገቡም እንደሚይዝ” ይናገራል። እዚህ ጋር የተጠቀሰው እቃ በእብራይስጥ አቆማዳ ማለት ነው። ይህም የእንባ ጎርፍና ወንዝ ነው። እግዚአብሔር እነዚህን እንባዎች ሊጠቀምባቸው ነው። ወንዙ እየመጣ ነው። እኛ እርስ በርሳችን በእውነት ስንዋደድ ያን ጊዜ ጎርፉ ይመጣል፤ ውሃውም ሞልቶ ይፈሳል።

ፍትህ እንደ ወንዝ፤ ፅድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፈሳል። (አሞጽ 5: 24) ያ ጎርፍ እየመጣ ነው። እንባችንን ወደምናፈስበት ወቅት ውስጥ መግባት አለብን፤ የፅድቅን እንባ፣ የትህትናን እንባ 
የይቅርታን እና የእምነትን እንባና ጩኸት እናልቅስ።

ማንኛውም የፀሎት ጥያቄ ካላችሁ በ @bezaconnect ይፃፉልን።