🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማስታወቂያ ዴስቲኒ:- ወርሃዊ የአዋቂ ወጣቆች ፕሮግራማችን ሰኔ 18 ቀን 2014 በቲኬ 8ኛ ፎቅ | Beza International Church

ማስታወቂያ

ዴስቲኒ
:- ወርሃዊ የአዋቂ ወጣቆች ፕሮግራማችን ሰኔ 18 ቀን 2014 በቲኬ 8ኛ ፎቅ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል። የዚህ ወር ዴስቲኒ በመቅደስ ገብረወልድ “በምንገነዘበው መኖር - መታለልን ማሸነፍ” በሚለው ርዕስ ይሆናል። መቅደስ የአሻጋሪ ትምህርት እና ማጎልበት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ እና በሽምግልና እና ግጭት አፈታት የፒኤችዲ እጩ ነች። በስልታዊ አስተዳደር፣ አማካሪነት እና አሰልጣኝነት ሰፊ ልምድ አላት። ስለዚህ ለመማር፣ ለመዝናናትና ለሕብረት ጊዜ ተነሳስታችሁ በሰዓቱ ተገኙ!

የአምልኮ ሰዓት:- የእሁድ የአምልኮ ሰዓት፦

የአማርኛ አገልግሎት፦ ከ2:45 - 4:45
የእንግሊዝኛ አገልግሎት፦ ከ5:15 - 7:15

የልጆች የሰንበት ትምህርት ፕሮግራም ፦

ዕድሜያቸው 2 እስከ 3 - ከአምልኮ በኋላ ወዲያውኑ ይጀምራል
ዕድሜያቸው 4 እስከ 11 - በ3:15 ሰዓት ይጀምራል
ዕድሜያቸው 12 እስከ 14 እድሜ - በ2፡45 ሰዓት ይጀምራል

የወጣቶች ፕሮግራም:- የቤዛ የወጣቶች ፕሮግራም ዕድሜያቸው ከ 15-23 ለሆኑ በየሳምንቱ እሁድ በአዲሱ ሕንጻ ቤዝመንት ከ 2፡45-4፡45 ይካሄዳል።

የደቀመዝሙርነት ትምህርት:- የደቀመዝሙርነት ትምህርት እሁድ በታበርናክል ከጠዋቱ 4፡45 እስከ 5፡45 ሰዓት ይካሄዳል። እሁድ መውሰድ የማይችል ማንም ሰው የደቀመዝሙርነት ትምህርት መውሰድ ከፈለገ በሌሎቹ ቀናት ፕሮግራም ስለምናዘጋጅ የምትፈልጉ እባካችሁ በዚህ ቁጥር "0907700007" አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ "@bezaconnect" ይመዝገቡ።

ያልተለመደ ፀሎት ላለፈው ወር በርትቶ እየቀጠለ ነው። በቤዛ ቤተክርስቲያን የተጀመረው የፀሎት እንቅስቃሴ በየሳምንቱ እየቀጠለ ስለሆነ ይምጡና ለሃገራችንና ለተለያዩ ጉዳዮች ማልዱ። በአዲሱ ህንፃ ምድር ቤት ለፀሎት በተዘጋጀው አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ ነው። ለኮቪድ የሚያስፈልጉት ጥንቃቄዎች ሁሉ በፀሎት ጊዜውም እየተከተልን ነው።
ያልተለመደ ፀሎት መርሃ-ግብር፦

ሐሙስ - ክቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት
ዓርብ - ከቀኑ 5:30 ሰዓት - 8:30 ሰዓት (የእህቶች ፕሮግራም)
ዓርብ - ከቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት (የእንግሊዘኛ ፕሮግራም)
ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰዓት-2 ሰዓት በዙም (ለመግባት ይህንን ኮድ ይጠቀሙ: 84216976202)
እሁድ - ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት – 2:30 ሰዓት

የአንድ ብሎኬት ለሕንፃው ፕሮጀክታችን ተጀምሯል፡፡ ከአሁድ ፕሮግራም ስትወጡ በ50 ብር ከተዘጋጁት ብሎኬቶች በመግዛት ራዕዩን ወደ ፍፃሜ እናምጣው፡፡