🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

 የሰኞ ጠዋት ንባብዎ ነፍሴን መለሳት መዝሙረ ዳዊት 23: 3 የዚህን ሳምንት መልእክት ያመጣው  | Beza International Church

 የሰኞ ጠዋት ንባብዎ

ነፍሴን መለሳት
መዝሙረ ዳዊት 23: 3

የዚህን ሳምንት መልእክት ያመጣው ፓስተር ዘሩባቤል መንግስቱ ነው።

ይህ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታዋቂ ምዕራፍ ነው፤ ምናልባት እኛም እነዚህን ጥቅሶች ብዙ ጊዜ ጠቅሰናቸው ይሆናል። ዛሬ እረኛው ነፍሳችንን እንደሚመልስ በሚናገረው ጥቅስ ላይ አተኩረን እንማራለን። የአማርኛውና ዋናው የአርማይክ ትርጉም የተጠቀሙት “ወደ ነበረበት ሁኔታ መመለስ” የሚለውን ፍቺ ሳይሆን “የወሰደውን መመለስ” የሚለውን ፍቺ ነው። ነፍስ እንዴት ትመለሳለች? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን። ወዴትስ ልትሄድ ትችላለች? ብለንም ልንጠይቅ እንችላለን።

በአካል አንድ ቦታ ሆነን ነፍሳችን ስለሌሎች ነገሮች እያሰበች ሌላ ቦታ ልትሄድ እንደምትችል ሁላችንም እናውቃለን። ታላቁ እረኛ ኢየሱስ ነፍሳችንን ከሄደችበት በመመለስ ሟች ስጋ ለባሽ ሊያደርገው በማይችለው ሁኔታ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን ሲመልሰን እናያለን።

ዛፉ
ኤርምያስ 17: 7- 8 “ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚታመን መታመኛውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው፤ በውሀ ዳር እንደ ተተከለ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፤ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም ቅጠሉም ዘወትር እንደለመለመ ነው በድርቅ ዘመን አይሠጋም ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”
 
መዝሙር 1: 1- 3 “በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ ሰው ብፁዕ ነው። ነገር ግን ደስ የሚሰኘው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል፤ እርሱም በወራጅ ውሀ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።” ሁለቱም ከላይ የተገለፁት ምንባቦች ስለዚህ  በውሀ ዳር ስለተተከለው ዛፍና እሱም እንዴት ፍሬያማ እንደሆነ ይናገራሉ። እያንዳንዳቸው ጥቅሶች የዚህ ዛፍ ባህሪ መገለጫ ስለሆነው መፅናት አንድ ጠቃሚና ቁልፍ የሆነ  ነገር ይሰጡናል።

ኤርምያስ ለፅናታችን ለመረጋጋታችን ምክንያቱ በጌታ ላይ ያለን መታመን መሆኑን ሲጠቅስ መዝሙር 1 ደግሞ የምንፀናውና  የምንረጋጋው ቃሉን ስናሰላስል መሆኑን ይናገራል። በመካከላቸው የሆነ ግንኙነት አለ፤ የመተማመን ችግር  እያጋጠመን ከሆነ ማሰላሰላችን የት እንዳለ መመርመር አለብን። የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰላችን በልባችን የነበረውን እምነት እንደገና ይመልሳል። እረኛው ነፍሳችንን የሚመልሳት በቃሉ ነው።

ምረቃ
በሉቃስ 4፡ 1- 11 ላይ ዲያብሎስ ኢየሱስን ሲፈትነው እናያለን። ኢየሱስም “ተፅፎአል” እያለ  በእግዚአብሔር ቃል ምላሽ መስጠቱን ቀጥሏል። በሦስተኛው ፈተና ሰይጣንም ቃል መጥቀስ ጀመረ። የሰይጣን ስትራቴጂ በእግዚአብሔር ቃልና በእምነት መካከል ክፍተትና ልዩነት መፍጠር ነው። ኢየሱስም በሌላ “ተፅፏል” ምላሽ ሰጥቶታል። እንደተተከለ ዛፍ የሚያደርገን ቃሉን ማወቃችን ሳይሆን በቃሉ ላይ ያለን እምነት ነው። በሁለቱ መሀከል ልዩነት አለ። ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል ከማወቅ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ማመን እንሻገር፤ በዚህም እንመረቅ።

የእምነታችን ሌላኛው ጎን
ሀና መፀነስ ስለማትችል በእጅጉ ተቸግራለች።1ሳሙ1 ነገር ግን ከጌታ ጋር ከተገናኘች በኋላ ፊቷ ላይ ዳግመኛ ሐዘን አለመታየቱን በ ቁጥር 18 ላይ ይናገራል። ከዚህ የነፍሷ መመለስ በኋላ ጌታ አሰባት። በዚህ የሚደንቀው መፀነሷ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የአገሪቱን መድረሻ የቀየረ ነብይ ወለደች። በእግዚአብሔር ላይ ባለው የእምነታችሁ ሌላኛው ጎን ምን እየጠበቃችሁ ነው? በተመለሰች ነፍሳችሁ እግዚአብሔር ምን ማድረግ ይፈልጋል?

ማንኛውም የፀሎት ጥያቄ ካላችሁ በ @bezaconnect ይፃፉልን።