🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

 የሰኞ ጠዋት ንባብዎ አቅማችሁን አሳድጉ የዚህን ሳምንት መልእክት ያመጡልን ፓስተር አንቶኒ ጆሮ | Beza International Church

 የሰኞ ጠዋት ንባብዎ

አቅማችሁን አሳድጉ

የዚህን ሳምንት መልእክት ያመጡልን ፓስተር አንቶኒ ጆሮጌ ናቸው።

ኤፌሶን 3፡20 ላይ እግዚአብሔር ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ እንደሚችል ይነግረናል። የዛሬው መልእክት ከማንኛውም ውሱንነቶች፣ ከትንሽ አስተሳሰቦች እንድንነቀነቅና የተሻሉና የበለጡ ቀኖቻችን አሁንም ከፊታችን እንደሆኑ ማመን ነው።

አቅም
የዌብስተር መዝገበ ቃላት አቅም የሚለውን ቃል ‘አንድን ነገር የመያዝ ወይም የማስተናገድ ችሎታ’ አድርጎ ይገልፀዋል። የበለጠ ለመለማመድ፣ አቅማችሁን ሆነ ብላችሁ ማስፋት አለባችሁ። ወደ ሰው ልጅ ስንመጣ ነገራችን ሁሉ ስትራቴጂያችንን ወይም ግባችንን  እውን የማድረግ አለማድረጋችን ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን  በልዩ ሁኔታ የሰጠን አቅም አለን። ማቴ 25፡ 15 “ ለእያንዳንዱ እንደችሎታው በመደልደል ለአንዱ አምስት ታለንት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱም አንድ  ታለንት ጉዞውን ቀጠለ" ይላል።

እያንዳንዱ አቅም ሊጨምር ወይም ሊሰፋ ይችላል። እግዚአብሔር ገና በሕይወታችን  ብዙ እንደሚሠራ እናምናለን። (ኢዮብ 42፡12) “እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት  ባረከ” ይለናል።

አቅም ከሌለህ ምን ይሆናል?
በ2ኛ ነገ 4፡1- 6 ባሏ ሞቶ በዕዳ ትቷት ስለነበረች አንዲት ሴት ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ጮኸች። በቤቷ ያለውን ነገር ጠየቃት፤ እርሷም ጥቂት ዘይት በአንዲት ማድጋ ውስጥ እንዳላት በመንገር መለሰችለት። ኤልሳዕም እንዲህ በማለት ጠየቃት፡- “እንግዲያው ሂጂና ከጎረቤቶችሽ ሁሉ ባዶ ጥቂት ሳይሆን ብዙ ማድጋ እንዲሰጡሽ ጠይቂያቸው” አላት። እሷም ማድጋዎችን ከሰበሰበችንና አንድም ማድጋ እስከማይቀር ድረስ ዘይቱን ከሞላች በኋላ ዘይቱ መፍሰስ አቆመ"ይላል።

አቅም እስካለ ድረስ ዘይቱ መፍሰሱን ይቀጥላል። አንዳንዶቻችሁ ተፅዕኗችሁ በአገር ደረጃ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በእናንተ እና በእናንተ በኩል ሊያደርግ የሚችለውን እየገደባችሁ ነው። እነዚያ ማድጋዎች ሞሉ። በመጨረሻም  ዘይቱ መፍሰስ አቆመ። ምክንያቱም ከዚያ በላይ አቅም አልነበራችሁም። ስለዚህ አቅምህን ማሳደግ አለብህ። (ኢሳይያስ 54: 2)

አቅሜን የበለጠ ለመጨመር ምን ማድረግ አለብኝ?

1. አማካሪ ይኑርህ፡- መካሪ ማለት መሄድ ወደምትፈልግበት ስፍራ ሄዶ ማድረግ የሚገባህን ያደረገ ነው። ሙሴ ራሱን ከዮቶር ጋር ሲያገናኝ የመሪነት አቅሙ ሰባ እጥፍ ጨምሯል። ጢሞቴዎስ ጳውሎስን፣ ኢያሱም ሙሴን ፈለገ። አንድ አማካሪ የበለጠ እንዳለ ያሳያችኋል። (ምሳሌ 15: 22)

2. ጥሩ ባላደራ ሁን፡- ታማኝ መሆን ብዙ ለመቀበል ብቁ ያደርገዋል። ማቴዎስ 25፡21 ላይ “በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ” ይላል። ገንዘባችሁን ወይም ጊዜያችሁን እንዴት እያጠፋችሁ ነው? ታማኝነት ዘርህን ያበዛል። እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ፊት አይቶ እንደማያደላ፤ ነገር ግን መርሆዎችን እንደሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ማቴዎስ 25: 29)

3. ደፍረህ ውጣ፡- እግዚአብሔር ከምቾት ቀጠናህ እንድትወጣ እየጠየቀህ ነው። ጎልያድህን ካልተጋፈጥክ እግዚአብሔር እንደቀባህ እንዴት ታውቃለህ? ከጀልባው ስትወጣ እግዚአብሔር ወደማታውቀው ቦታ ይወስድሃል! (ማርቆስ 9: 23)

4. ተማሪ ሁን፡- መፅሐፍትን አንብብ! ትምህርት ቤት ገብተህ ተማር! መጥረቢያህን ስትስል አቅምህን ትጨምራለህ። አንዳንዶቻችን ለማደግ አእምሯችንን ማስፋት አለብን።

5. ልግስና፡- ወደ እግዚአብሔር ባደግክ መጠን ያለህ ነገር ያንተ እንዳልሆነ፤ ነገር ግን ባለአደራ እንደሆንክ ትገነዘባለህ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ሕብረት እየጨመረ ሲሄድ የኪስ ቦርሳችን እንዲሁ መከተል አለበት። ሉቃስ 6፡ 38 ላይ “ስጡ፤ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ስለሚሰፈርላችሁ፣ ጫን በተደረገ፣ በተነቀነቀና በተትረፈረፈ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ በዕቅፋችሁ ይሰጣችኋል። ” የበለጠ ለመቀበል የምትሰጠው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ብቻ ነው።

ማንኛውም የፀሎት ጥያቄ ካላችሁ በ @bezaconnect ይፃፉልን።